የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የእግዚአብሔር ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡ 2 ቆሮ 13 14
ከኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት በፊት ለደቀመዛሙርቱ ያለእርሱ መኖርን እንዲለማመዱ ልነግራቸው ሞክረው ነበር፡፡ እንደሚሄድ ነገራቸው አባት ሌላ አጽናኝ እንደምልክላቸው በእነርሱ ውስጥ የምኖር መንፈስ ቅዱስ የሚመክራቸው፣ የሚረዳቸው፣ የሚያበረታታቸው፣ የሚማልድላቸው፣ እንደጠበቃ የሚሟገትላቸው ስለኃጥያት ስለጽድቅና ስለፍርድ እንዲወቅሳቸው ለጠበቃ ኅብረት ወደ እነርሱ ይመጣል ወደ እውነት ሁሉ ይመራቸዋል፣ ሁሉን ነገር ወደ እነርሱ ከክርስቶስ እንደ ወራሽ ያስተላልፋል፡፡ (ዮሐ 16 7-15፡ ሮሜ 8 17 ተመልከት)
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የላከልን እኛ ከእርሱ ጋር ግንኙነታችን የጠነከረ እንድንሆንና እርሱ ለእኛ ያቀረበውን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል እንድንችል እንደሆነና ለእኛ አሳቢነቱን ማየት ትችላለህ፡፡ እኛ ከፈቀድንለት እርሱ ያመቻቸናል፣ ይመክረናል፣ ያደርግልናል፡፡ የእርሱን ድምፅ መስማት አለብን፡፡ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ እኛን የሚያገለግልበት መንገድ፣ የሚመራን፣ የሚረዳን ለእኛ በመናገር ስለሆነ ነው፡፡
ለሕይወታችን መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔርም እርሱን ሰጠን ከእርሱ ጋር ያለን ኅብረትም እኛ በፈለግነው መጠን እየጠበቀና እየጠለቀ የሚሄድ ነው፡፡ ከሁሉም ማድረግ ያለብን ነገር ጊዜ በመውሰድ ከእርሱ ጋር በመሆን እንዲናረን በመጠየቅ ልባችንን ለቃሉ በመክፈት በፊቱ መሆን አለብን፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ግንኙነት አንተ በፈለከው መጠን እየጠበቀና እየጠለቀ ይሄዳል፡፡