መውጣትና መፈለግ

መውጣትና መፈለግ

ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ እግዚአብሔር ግን ርምጃውን ይወስንለታል። – ምሳሌ 16:9

ሰዎች በጣም በተደጋጋሚ የእግዚያብሔር ፈቃድን እንዴት ማወቅና ማግኘት እንደሚችሉ ይጠይቁኛል አንዳንዶች ለበርካታ ዓመታት መለኮታዊ ድምፅን ለመስማት አልያም አቅጣጫ ለመቀበል ይጠባበቃሉ፡፡ ነገርግን የእግዚያብሔርን ድምፅ በልባችን ማድመጥ የሁልጊዜም መንፈሳዊ ተግባራችን ሲሆን ከዚያ በላይ ተጨባጭና ተግባራዊ ነው፡፡ እኔም እንዲወጡና እንዲያገኙት ነው የነገርኳቸው፡፡

ከእግዚያብሔር ጋር በነበረኝ የመጀመሪያ ጉዞዎቼ ላይ እግዚያብሔርን ማገልገል እፈልግ ነበር፤ ጥሬም እንዳለኝ አምን ነበር ነገርግን ምን ማድረግ እንዳለብኝ አልገባኝም ነበር፡፡ ስለዚህም በአቅራቢያዬ የሚገኙትን የተለያዬ ዕድሎችን ለመሞከር ጥሬያለሁ፡፡ ለእኔ የሚሆነውን ትክክለኛውን መንገድ እስከማገኝ ድረስ በጣም በርካታ መንገዶችን ሞክሪያለሁ፡፡በመጨረሻም ለሰዎች እግዚያብሔርን ቃል ለማካፈል እድል ባገኘሁበት ጊዜ መገናኘት ችያለሁ፡፡ በማስተማር ውስጥ ደስተኛ መሆን ቻልኩ በዚህም እግዚያብሔር ይህንን ስጦታ በልቤ እንዳኖረው ለመረዳት ቻልኩኝ፡፡ከዚህ በኋላ እግዚያብሔር በምን ውስጥ እንዳገለግለው እንደጠራኝ አወኩኝ፡፡

የእግዚያብሔርን ፈቃድ በህይወታችን ውስጥ ለማወቅ የሚያስችለን ብቸኛው መንገድ እኔ እንደምጠራው መውጣትና መፈለግ ነው፡፡አንድ የሆነነገር ላይ እየጸለያችሁ ከሆነና ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ካልገባችሁ በእምነት አንድ ደረጃ ፈቅ በሉ፡፡ስህተት ስለመስራት መፍራት የለባችሁም በእምነት መንቀሳቀስ ከጀመራችሁ እግዚያብሔር ይመራችኋል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ እንዳንዱን መንገዶቼን እንደምትመራኝ አምናለሁ ስለዚህም አንተ የምትፈልገውን ለመሆን ምንም ሳልፈራ በመውጣት እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon