መዝራት እና ማጨድ

መዝራት እና ማጨድ

አትሳቱ ፤ እግዘኢአብሔር አይዘበትበትም፡፡ ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ – ገላቲያ 6፡7

መጽሀፍ በግልጽ የዘራነውን እንድምናጭድ ይናገራል፡፡ ቃል በቃል ከግብርና እና ተክል ከመትከል ጋር የተገናኘ ነው፡፡ በርከት ያሉ ሰዎች ገንዘብን በልግስና ከመስጠት ጋር ያገኛኙታል፡፡ ይህ መርህ ሌሎችን በምን አግባብ ማስተናገድ እንዳለብ እንደሚናገር ታውቃላችሁ?

አቋማችንን ንግግራችን በየቀኑ የምንዘራቸው ዘራችን ናቸው ፤ በግንኙነታችንና በሁኔታዎቻችን ውስጥ የምንሰበስበው ፍሬም በዚሁ ዘር ይወሰናል፡፡

ዲያቢሎስ ራስ ወዳድ ፣ ታማኝ ወዳጆቻችን የማይጠቅሙ እንደሆኑ ፣ በቤተሰብ መካከል የጠብ ቃላትን መዝራት እና በአለቆቻችን ላይ በክፋት እንድናስብ ወዘተ. ማድረግ ይወዳል፡ ዲያቢሎስ በሁሉም ግንኙነታችን እና ጉዳዮቻችን ላይ ይሄን መጥፎ ዘር እንድዘራ ይፈልጋል።

በርከት ያሉ ሰዎች ባለተገባ መንገድ ጠባያቸውን ያሳዩ እና ሰዎች ለምን በማይገባ መንገድ አስተናገዱን ብለው ይገረማሉ፡፡ መልሱ ቀላል ነው ፤ የዘሩትን እያጨዱ ነው፡፡

እስኪ ልጠይቃችሁ ፤ ምን እየዘራችሁ ነው ዛሬ ? በእግዚአብሔር ጸጋ ፍቅርን ፣ ይቅርታን ፣ መልካምነትን ፣ ትዕግስትን በየትኛውም ሁኔታዎች እና ግኑኝነታችሁ መዝራትን ምረጡ ፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን እንድትቀበል በሚፈልገው አግባብ ሰዎችን ስትቀበል ብዙ ብርታትንና ፣ መልካምነትና እና አጥጋቢ ውጤቶችን ሕይወት በሙላት ታጭዳለች፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ መልካም ዘርን በመዝራ መልካም ነገር ማጨድ እሻለሁ፡፡ ራስ ወዳድ ሆኜ ከመኖር ይልቅ በጎነትንና ፍቅርን በግኑኝነት ውስ ባሉ ሰዎች ሕይወት ውስጥ እንድዘራ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon