እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ኀይላቸውን ያድሳሉ፤እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፣ ይሮጣሉ አይታክቱም፣ ይሄዳሉ አይደክሙም። – ኢሳ 40፡31
ሰዎች ብዙ ጊዜ “በእርግጠኝነት ከእግዚአብሔር እየሰማሁ ይሁን ወይም እራሴ እየፈጠርኩ በምን ላውቅ እችላለሁ?” ብለው ይጠይቁኛል፡፡
መልሱ መጠበቅን መማር ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ትልልቅ ውሳኔዎች ሲኖሩብን ብዙ ጊዜ መፍጠን እንፈልጋለን፡፡አንድ ነገር አሁኑኑ ማድረግ አለብን!ነገር ግን እግዚአብሔራዊ ጥበብ ልናደርገው የሚገባው ነገር እና መቼ ልናደርገው እንደሚገባ ግልጽ ሆኖ እስኪታየን ድረስ እንድንጠብቅ ይነግረናል፡፡
እኛ ሁላችን ትንሸ ወደ ኋላ መለስ ብለን ሁሉንም ሁኔታ እግዚአብሔር እንደሚያየው እይታ የማየት አቅም ማዳበር አለብን፡፡የዚህን ጊዜ ብቻ ነው እርሱ በሚፈልገው መንገድ ውሳኔ መወሰን የምንችለው፡፡
በመጠበቅ ውስጥ ጥንካሬ ይገኛል። ጌታን ስትጠብቁት ሳላችሁ በመንፈሳችሁ ውስጥ እናንተ እንዳደርጉ ይፈልጋል ብላችሁ የምታስቡትን ሳይሆን ጌታ ምን እንድታደርጉ እንደሚፈልግ ይታወቃችኋል፡፡
ማንኛውም አይነት ከባድ ውሳኔ የሚያስፈልገው ነገር ሲያጋጥማችሁ የምትጸጸቱበትን እርምጃ ከመውሰዳችሁ በፊት ግልጽ መልስ እስክታገኙ ድረስ መጠበቅ ጠቢብነት ነው፡፡ምቾት ሊነሳችሁ እና መፍጠን ልትፈልጉ ትችላላችሁ ከእግዚአብሔር እውቀት እና ጥበብ በላይ ጫና እንዲያይል አትፍቀዱ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ በጊዜው ግለት ውስጥ ተይዤ የምጸጸትበትን ውሳኔ መወሰን አልፈልግም፡፡በየዕለቱ አንተን መጠበቅ እንዳለብኝ አስታውሰኝ፡፡ሊከብድ ይችላል ነገር ግን ለአንተ ጥበብ እና ዕውቀት መጠበቅ ይገባዋል፡፡