መጥፎ ልማዶችን መተው

ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ – ሮሜ 12፡21

ክርስቶስ ጋር ያለንን ግንኙነት ስንጀምር እግዚአብሔር እንደፈጠረን አይነት የእግዚብሔር ህዝብ የመሆንን የዕድሜ ልክ ጎዞ ነው የጀመርነው፡፡በሂደት ድካማችንን እንዴት እንደምናሸንፍ እና በእግዚአብሔር ጥንካሬ እንዴት እንደምንኖር እንማራለን፡፡ይሄም ማለት መጥፎ ልማዶችን መተውን መማር ማለት ነው፡፡

ለአመታት ነገሮች በእኔ መንገድ ባልሄዱ ቁጥር የመናደድ ልማድ ነበረብኝ፡፡ምናልባት ይሄ የእናንተ መጥፎ ልምድ ላይሆን ይችላል፡፡ምናልባት እናንተ ታሙ፣ጥሩ ይልሆኑ ቃላቶችን ትጠቀሙ ይሆናል፣ከመጠን በላይ ቡና ትጠጡ፣ለረጅም ጊዜ ቲቪ ትመለከቱ ወይም በማያስፈልጓችሁ ነገሮች ላይ ገንዘብ ታባክኑ ይሆናል፡፡መጥፎው ልማዳችሁ ምንም ሆነ ምን ልትተዉት ትችላላችሁ፡፡

መጥፎ ልማድን መተው ቀላል ነው እያልኩ አይደለም ነገር ግን መጥፎ ልማዶችንን ላይ ስልጣን እንዲኖረን የእግዚአብሔር ፍላጎት ነው፡፡በስሜቶቻችን “እንድንነዳ” አይፈልግም-ይልቁንስ ድል እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡

መጥፎ ልማድን መተው አንዱ ከሌላው ጋር ተከታታይነት ያላቸውን ጥሩ ምርጫዎችን መምረጥን ይጠይቃል፡፡ብዙዎቻችን ይሄንን ለማድረግ የምንሞክረው በራሳችን ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ነው ፡፡ ነገር ግን ያለ እግዚአብሔር ዕርዳታ እግዚአብሔርን ማስደሰት እንደማንችል እንረዳለን።

አምፕሊፋይድ የተባለው የመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም መንፈስ ቅዱስን “ዝግጁ” ይለዋል. ድንገት ችግር ውስጥ ከገባችሁ እና ዕርዳታ ከፈለጋችሁ ሁሌም ዝግጁ ነው፡፡ነገር ግን ሳይጋበዝ አይገኝም፡፡ለዕርዳታ ልትጠሩት ይገባል፡፡

ሮሜ 12፡21 ሲናገር ክፉን በመልካም አሸንፉ ይላል፡፡በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ካሉ ትልልቅ ሚስጥሮች አንዱ ነው፡፡ የውድቀት ፍርሃት ላይ ከማተኮር ይልቅ በእግዚአብሔር እና በድላችሁ ላይ ስታተኩሩ ትክክለኛውን ውሳኔ መወሰን በጣም ይቀላል፡፡

በመንፈስ ለመመላለስ ዛሬ ምረጡና መጥፎ ልምዶችን አሸንፋችሁ በድል ኑሩ!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ከመጥፎ ልምዶቼ ጋር መኖር በቅቶኛል፡፡እንደ አለቃ ሊቆጣጠሩኝ በሚፈልጉት ፈተናዎቼ ላይ ለመሰልጠን አሁን እመርጣለሁ፡፡ቅዱስ መንፈስህን ወደ አዲስ እና የተሸሉ የህይወት ልምምዶች እከተለዋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon