መጸለይ ከዚያም ማቀድ

መጸለይ ከዚያም ማቀድ

‹‹በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል›› (ምሳሌ 19፡21) ።

የእግዚአብሔር ቃል በግልጥ እንደሚሳየን የእርሱን ድምጽ መስማትና ጆሮችን ከእርሰ ጋር ላለን ቃልኪዳን የተሰጠ እንዲሆን ያስፈልገናል፡፡ እርሱ ጆሮአችንን እንዲቀድስማ እንዲገርዘው መፍቀድ አለብን፡፡ ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብን ያሳየናል ነገር ግን እርሱ የሚያሳየንን ዕቅዱን ስለማንፈልገው አናደርገውም፡፡ እርሱ ሲናገር የሰማነውን ነገር ላለማድረግ መንፈሳዊ መከላከያዎችን እቀረብን ለማስመሰል ጭምር እንሞክራለን፡፡ የእግዚአብሔርን እውነት እንዳንቀበል የእኛ ስጋዊ ፍላጎቶቻችንና መሻቶቻችን እንቅፋት ይፈጥሩብናል፡፡

ከእውነት ጋር ፊት ለፊት ልንጋፈጥ እንችላለን እናም አሁንም እውነትን ለመቀበል አንፈልግም፡፡ ብዙውን ጊዜ ከራሳችን ህይወትና ትኩረቶቻችን ይልቅ ለሌሎች ህይወትና ትኩረቶች ላይ ትኩረት ለማድረግ ስንነሳ እውነትን ለማስተናገድ በጣም ቀላል ይሆንልናል፡፡ ህይወታችን እንድትጓዝበት የምንፈልገው መንገድ ለመስጓዝ እቅድ አለን፤ እንዲሁም በህይወታችን እንዲሆን ያቀድነው ዕቅድ የሚፈጸምበት መንገድም አለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔር የእርሱን እቅድ ከመስማትና እርሱ በእኛ ሊያደርገው ያለውን እንዲፈጽም ከመጠየቅ ፈንታ የእኛን የምፈልገውን ዕቅድ እንዲሰማልንና እንዲደርግልን እንፈልጋለን፡፡ እኛ አስቀድመን አቅደን ከዚያም እግዚአብሔር ወደሥራ እንዲተገብረው መጸለይ ፈንታ ማድረግ የሚገባን አስቀድመን መጸለይ ከዚያም ማቀድ አለብን፡፡ የእግዚአብሔርን እቅድ መስማ፣ እርሱን መከተልና ሁልጊዜ ስኬትን እንዲሳካልን ደደርጋል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ የእግዚአብሔርን እቅድ ማስቀደም ከዚያም ያንተን እቅድ ማስከተል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon