ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ታመን

ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ታመን

አቤቱ፣ አንተን ታመንሁ ለዘለዓለም አስፍር ለጽድቅህም አድነኝ፡፡ መዝ 31÷1

በሕይወቴ እግዚአብሔር ሙሉ ቀን ሰርቼ ጥሩ ገቢ የማገኝበትን ሥራ ትቼ ፀጥ ብዬ እንዳፍር ሲነገረኝ አስታውሳለው፡፡ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መነጋገር ጀመረ፡፡ አርፈሽ እቤት በመሆን እራስሽን ለአገልግሎት አዘጋጂ ይለኝ ነበር፡፡

እኔ ቶሎ ብዬ ሥራዬን ለመልቀቅ ስል ፈራው ፈጥኜ ለመታዘዝ አልቻልኩም፡፡ በኋላ ግን ይህ ድምፅ ከእግዚአብሔር መሆኑን እንዴት አውቃለሁ የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ፡፡ እግዚአብሔር ግን ከእኔ ጋር መናገሩን ቀጠለ፣ እኔም በመጨረሻ ከእርሱ ጋር ድርድር ጀመርኩ፣ እኔም ሙሉ ጊዜዬን ሳይሆን ግማሽ ቀን እየሠራው ግማሽ ቀን እንዳገለግል ሃሣቤን መግለፅ ጀመርኩ፡፡

ስለዚህ የግማሽ ቀን ሥራ ለመሥራት ግማሽ ቀን ለማገልገል ጀመርኩ ምክንያቱም ለሙሉ ቀን አገልግሎት እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ ለመታመን ስለፈራው፡፡ ከዚያ እኔና ባለቤቴ ዳዊት ገብያችን እንደ ድሮ መሆን ስላልቻልን እኔ በትንሽ ገንዘብ መኖር እንደምችል ወሰንኩ፡፡ ውድ የሆነ የውጭ አካሄድን ሠረዝን ነገር ግን አስፈላጊ ወጭዎችን መክፈል ቻልን፡፡ እኔም ብዙ ጊዜ ለአገለግሎቴ ዝግጅት አገኘው፡፡ ይህ ጥሩ ዕቅድ መሠለን ነገር ግን የእግዚአብሔር እቅድና አላማ አልነበረም፡፡

እግዚአብሔር የእራሴ የሆነ ዘዴና መንገድ ትቼ እንድወጣ ስላስተማረኝ የግማሽ ቀን ሥራውንም ሙሉ በሙሉ በመተው ወጣው፡፡ እኔ ታታሪ ሠራተኛ ስለነበርኩ ከሥራ ተባርሬ አላውቅም፡፡ እኔ ያለሁበት ሁኔታ ደስ ባያሰኘኝም አሁን እግዚአብሔር በፈለገኝ ቦታ በመሆን ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መደገፍ ቻልኩ፡፡

ያለምንም ሥራ ለሚያስፈልገኝ ጥቃቅን ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔርን መታመን ተማርኩ፡፡ ለስድስት አመት በየወሩ ለምንከፍለው ወጭዎች የመለኮትን ጣልቃ ገብነት አይተናል፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ የእግዚእሔርን ታማኝነት አግኝቻለሁ፡፡ የእግዚአብሔር አቅራቦት ብዙ ልምምድ ስላስተማረን ዛሬ ለምናንቀሳቅሰው ዓለም አቀፍ አገልግሎት የሚውል ሃብት በእርሱ ለመታመን እምነት ሆኖናል፡፡ እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ እንድትተማመንና የማያዋጡህን የራስህን ዘዴ እንዳትሞክር አበረታታለው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ድርድር ድል አይሰጥም.

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon