ሚዛናዊ ሁን

ሚዛናዊ ሁን

በደንብ ሚዛናዊ (ልከኛ፣ አእምሮ ያለው) ሁን፣ ሁል ጊዜ ንቁ እና ጠንቃቃ ሁን; ምክንያቱም ጠላትህ ዲያብሎስ የሚይዘውን እና የሚውጠውን ሰው ፈልጎ [በከባድ ረሃብ] እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያህ ይዞራልና። (1 ጴጥሮስ 5: 8)

መንፈስ ቅዱስን መስማት በሁሉም የሕይወታችን አቅጣጫ ሚዛናዊ ያደርገናል። በጣም ብዙ ገንዘብ ስናወጣ ወይም በቂ ወጪ እንዳላወጣን፣ አብዝተን ስናወራ ወይም በቂ በሆነ መጠን ሳናወራ ስንቀር፣ ወይም ብዙ ስናርፍ ወይም በቂ እረፍት ሳናገኝ ስንቀር መንፈሱ ይነግረናል። ምንጊዜም እንድን ነገር ከልክ በላይ ወይም ከልክ በታች ስናደርግ ሚዛን እያጣን ነው።

ዛሬ ያነበብነው ክፍል ሰፅጣን ዕድል ፈንታ እንዳያገኝ ሚዛናዊ መሆን እንዳለብን ይናገራል። በስራዬ በኩል ከነበረኝ ሚዛን ማጣት የተነሳ ሰይጣን ለዓመታት በህይወቴ ዕድል ፈንታ አግኝቶ ነበር። ሕይወቴ በሙሉ ሥራዬን ማዕከል ያደረገ መሆን እንዳለበት ይሰማኝ ነበር። አንድ ነገር እየሰራሁ እና እያሳካሁ እስካለ ድረስ ዲያቢሎስ በእኔ ዕድል ፈንታ እንዳገኘ የሚሰማኝ የጥፋተኝነት ስሜት አልነበረም። ነገር ግን ያ ሁልጊዜ የመስራት ፍላጎት ከእግዚአብሔር አልነበረም፤ በሕይወቴ ቅዱስ ወደሆነ ሚዛናዊነት አልገፋኝም ነበር። ሥራ ጥሩ ነገር ነው፤ ነገር ግን ማረፍ እና መደሰትም ያስፈልገኝ ነበር።

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ለመስማት በምትፈልግበት ጊዜ በህይወትህ ውስጥ ሚዛናዊ ያልሆነን ማንኛውንም ቦታ እንዲያሳይህ ጠይቀው ደግሞም ማስተካከያዎችን ለማድረግ ከእሱ ጋር አብረህ ስራ። በሕይወታችን ውስጥ ብዙ የሚያጎመጁን ነገሮች አሉ ስለሆነም ከሚዛን ለመውጣት ቀላል ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚህ ዙሪያ እኛን ለመርዳት ሁልጊዜ ይገኝልናል። በቀላሉ ማንኛውንም ነገር ከመጠን በላይ ወይም በቂ ባልሆነ መጠን እየሰራህ እንደሆነ ጠይቀው እና እርሱ የሚመክርህን ለውጦች አድርግ።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ በእግዚአብሔር እርዳታ ሚዛናዊ ሁን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon