ማህበራዊ ፍትህ

ማህበራዊ ፍትህ

እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወዳል፡፡ – ዘዳ 10፡18

አንድ ሰው በችግር ውስጥ እንዳለ አውቆ ምንም ለማድረግ አለመቻል ስህተት ነው፡፡ላብራራው…

ከጥቂት ጊዜ በፊት ጌታ ለተጨቆኑት ፍትህን እንዲያገኙ እንድሰራ ምን ያህል እንደሚፈልግ ገልጦልኝ ነበር፡፡በክርስቶስ አካል ውስጥ ላሉ ሁሉ የጠራቸው ጥሪ አካል ነው፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን ህጉን ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ አባት የሌላቸውን፣መበለቶችን፣የተጨቆኑትን፣ድሆችን፣ብቸኞችንና የተረሱትን የሚረዱ ሰዎችን እየፈለገ ነው፡፡

በሙሴ በኩል ሲናገር ማንኛውንም አባት የሌለው ልጅም ሆነ መበለት አትበድሉ (ዘጸ.22፡22)፡፡እግዚብሔር ስለማያዳላ ፍትህን አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወዳል፡፡ (ዘዳ.10፡18)፡፡እግዚአብሔር ህዝቡን መጻተኞችን፣መበለቶችንና አባት የሌላቸውን የሚመግቡ ከሆነ የእጆቻቸውን ስራ እንደሚባርክ ነግሯቸዋል(ዘዳ.14፡29ን ይመልከቱ)፡፡

በጣም ብቸኛ እና የተረሱ ከሚባሉት ሰዎች መሀከል ጥቂቶቹ ለመኖር ሲባል ወደ ሴተኛ አዳሪነት ስራ ውስጥ እንዲገቡ የተገደዱ ሴት ልጆች፣ወላጆቹን በኤድስ ያጣ ልጅ፣በእስር ክፍሉ ውስጥ ዕለት ተዕለት የሚያሳልፈው እስረኛ፣መንገድ ላይ የሚኖረው ቤት አልባ ሰው…ሌላም ብዙ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡

ይሄ ሁሉ ነገር ከአዕምሯችሁ በላይ ሆኖ ታዲያ ስለዚህ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ? ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ፡፡ምንም እንኳ ለሁሉም ነገር መፍትሄ ማምጣት ባልችልም የአንድን ሰው ስቃይ መቀነስ ከቻልኩ ልዩነት እያመጣሁ መሆኑን እግዚአብሔር አስተምሮኛል፡፡

እባካችሁ እናንተ ልትሰጡ የምትችሉት ነገር በቂ እንዳልሆነ አታስቡ፡፡የተጎዱ፣የተሰበሩ፣የተራቡ እና ቤት የሌላቸው ሁሉም በዙሪያችን አሉ፡፡ዛሬ ትረዷቸዋላችሁ?


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ድሆች እና ብቸኛ የሆኑትን ልትረዳቸው እንደምትፈልግ ግልጽ ነው፡፡ለፍትህ የሚሆን ያንተን ልብ ስጠኝ እንድረዳቸው የምትፈልጋቸውን የተጎዱ እና የተሰበሩ ሰዎች አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon