በምስጋና ወደ ደጆቹ፣በውሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤አመስግኑት፤ስሙን ባርኩ፤ – መዝ 100፡4
በኤፌሶን 4፡29 ላይ ሐዋሪያው ጳውሎስ የማይረባ ቃል ቃላት ከአፋችሁ አይወጣ ብሎ ያዘናል፡፡በአንድ ወቅት ይሄ ቃል ማጉረምረምን እንደሚያጠቃልል አላውቅም ነበር፡፡ከዛ በኋላ ግን ማጉረምረም እና መነጫነጭ ህይወታችንን እንደሚበክሉት ተምሬያለሁ፡፡
በአጭሩ እና በቀላሉ ማማረር ሀጢያት ነው! ሰዎች ላይ ብዙ ችግር ከማምጣቱም በላይ የሚሰማውን የማንኛውንም ሰው ደስታ ያጠፋል፡፡
ራሳችንን መንገድ ሲዘጋብን ወይም የታክሲ ሰልፍ ስንጠብቅ ትዕግስታችን የሚያልቀው እና ማማረር የምንጀምረው በምን ፍጥነት እንደሆነ መጠየቅ አለብን፡፡የጓደኞቻችንና የቤተሰቦቻችንን አባሎች ጥፋት አይተን ለመጠቆም ምን ያህል ፈጣን ነን? ስራ ስላለን እግዚአብሔርን ልናመሰግን ሲገባን ስለስራችን እናማርራለን?
መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር ወደ እግዚአብሔር አደባባዮች በምስጋና እና በአምልኮ መግባት አለብን ይላል፡፡እኔ እና እናንተ የምስጋና ህይወት መኖርን የየዕለት ግባችን ልናደርገው ይገባናል፡፡በተቻለ መጠን አመስጋኝ እና መልካሙ ነገር ላይ የምናተኩር ልንሆን ይገባናል፡፡
ማታ ወደ አልጋችሁ ስትሄዱ ልታመሰግኑበት የሚገባውን ነገር ሁሉ አስቡ፡፡ ጠዋት ስትነሱ መጀመሪያ የምታደርጉት ነገር ይሁን፡፡ ለትናንሽ ነገሮች ወይም አብዛኛውን ጊዜ ትልቅ ቦታ ለማትሰጧቸው እንደ መኪና ማቆምያ ቦታ ማግኘት፣በጠዋት ለስራ መንቃት፣ለምግብ፣ለቤተሰባችሁ ሌላም ትንንሽ ለሚመስሉ ነገሮች እግዚአብሄርን አመስግኑ፡፡ ውድቀት ሲያጋጥማችሁ ተስፋ አትቁረጡ አቋርጣችሁም አትሂዱ፡፡አዲስ ልምድ አድርጋችሁ እስክታዳብሩት ድረስ እና የምስጋናን ህይወት እስክትኖሩት ድረስ ቀጥሉ፡፡
አመስጋኝነታችሁን ለማሳየት ቸር ሁኑ፡፡ ከጌታ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ያጣፍጠዋል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ከአሁን ጀምሮ የአመስጋኝነት አመለካከት ይዤ መኖርን እፈልጋለሁ! ስለምትወደኝ እና ስለምትባርከኝ አመሰግናለሁ፡፡በህይወት ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች እያየሁ ማመስገን እንድችል እርዳኝ፡፡