ምንም የሚለያይ ግድግዳ የለም

ምንም የሚለያይ ግድግዳ የለም

«… በዚያም የግሪክ ሰው አይሁዳዊም የተገረዘም ያልተገረዘም አረማዊም እስኩቴስም ባሪያም ጨዋ ሰውም መሆን አልተቻለም፥ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፥ በሁሉም ነው» (ቆላ.3፡11)።

በክርስቶስ እግዚአብሔር ሁሉንም ልዩነቶች አስወግዶ አንድን አዲስ ፍጥረት ፈጥሮና ሁላችንም በእርሱ አንድ ሆኗል። በተግባራዊ ቃላት ይህም ማለት ምንም ማድረግ አቅም በሌለን ማንኛውም ጉዳይ ላይ እግዚአብሔር ኃላፊነትን ስለሚወስድ በእርሱ መታመን እንዳለብንና በእኛ ውስጥ ማንኛውንም መልካም የሆነውም ነገር ሁሉ እንደ ስጦታ ከእርሱ የተሰጠ ነው ወይም ማንኛውንም እኛ የምናደርገው መልካም ነገር ሁሉ ከእርሱ የተቀበልነው። ሁሉም ነገር በርሱ የሆነ ነው። እኛም በእርሱ ከእግዚአብሔር ጋር መልካምን እናደርጋለን፣ የእኛ ህይወት በእርሱ ነው፣ ደስታችንና ሰላማችን በእርሱ የሆኑ ናቸው። ሁሉም ወደ እርሱ፣ ለእርሱ፣ በእርሱና ከእርሱ የሆኑ ናቸው (ሮሜ 11፡36)።

እኛ ራሳችንን ከሌላ ከማንም አካል ጋር ከእንግዲህ አናወዳድርም። እነርሱ ስለሚያደርጉት ነገር እኛ ማድረግ ባይሆንልን ምንም አይደለም ምክንያቱም የእኛ ክብርና ዋጋ በእርሱ ብቻ ነው። እኛ ከውድድርና ከንጽጽር ህይወት ነጻ ነንና ራሳችንን የቻልን ሙሉ ሰው እንድንሆን አቅም ሰጥቶናል። ልትሆን የምትችለው ዋናውን አንተነትህን ሁን። ከእንድ ነገር በአጥጋቢነት ለመሥራት የምትችል ከሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፣ አንዲሁም የማትበቃ ሆነህ ከተገኘህ አሁንም አመስግነው ለማንኛውምእርሱ ይወድሃልና እርሱ ሊሆን ስለሚያስፈልገው ነገር ኃላፊነትን ይወስዳል።

ይህ እውነት ወደ እግዚአብሔር እረፍት እንድትገባና የራስህን ህይወት መገለል ሀዘን ወይም ከዚህ ቀደም ፈጽሞ ያልሆንከውን አንድ ነገር ለመሆን ህይወትህን ልታሳልፍበት የምትሞክረው ሁሉ ለማስወገድ ፍቀድ። የእግዚአብሔርን ድምጽ የምትሰማ ከሆነ አንተ ልዩ ሰው እንደሆንክ በትክክል እንዲናገርህ እርሱን ስማው፣ ከሌላው ሰው ጋር ራስህ ለማነጻጸር ምንም አያስፈልግህም። ሁሉም የሚለያይ ግንብ በክርስቶስ ተወግዿልና በእርሱ እኛ አንድ ነን።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ሌላውን ሰው ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር በፍጹም አይረዳህም፤ ነገር ግን አንተ መሆን የምትችለውን ሁሉንም እንድትሆን ይረዳሃል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon