
እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው። (ሰቆቃወ ኤርሚያስ 3:25)
ስለምንፈልገው እና ስለምንመኘው ነገር ከጸልይን እና እግዚአብሔርን ከጠየቅን በኋላ መጠባበቅ አለብን። በተስፋ የተሞላን መሆን አለብን፤ ይህም በደስታ እና በእርግጠኝነት አንድ በጎ ነገር እንደሚሆን መጠባበቅ ማለት ነው ። በልጅነቴ እና በለጋ ዕድሜዬ ለዓመታት ከተበሳጨሁ በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የተጨቆኑ እንደሚላቸው ሆንኩ። (ምሳሌ 15፡15 ን ተመልከት) ። ያ ማለት አብዛኛውን ጊዜ መጥፎ ዜና እጠብቅ ነበር ማለት ነው። ብዙ ሰዎች ዳግመኛ መጎዳት ስለማይፈልጉ መልካም ነገር መጠባበቅን ከመፍራት ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል ብዬ አምናለሁ። እግዚአብሔር እርሱ መልካም ስለሆነ ሁሉም ሰው ከእርሱ መልካም ነገሮችን በኃይለኛ ሁኔታ እንዲጠባበቅ ይፈልጋል።
እንዲሁ ዝንጉ ሰው አትሁን። ዝንጉ ሰው መልካም ነገሮች እንዲሆኑ የሚፈልግ ሰው ነው ነገር ግን የሚሆነውን ለማየት ከመጠበቅ በስተቀር ምንም ነገር አያደርግም። ምንም እንኳን የዛሬው ክፍል እንድንጠብቅ ቢነግረንም፣ እንድንጠባበቅም ይነግረናል። እግዚአብሔርን እንዲሠራልኝ እየጠበቅሁት ቅዱሳት መጻሕፍትን ጮክ ብዬ ማወጅ እፈልጋለሁ። ተስፋዎቹን ያስታውሱኛል፣ ያበረታቱኛልም። የእግዚአብሔር ቃል በመፍጠር ኃይል የተሞላ ነው ደግሞም በእምነት ሲነገር አዝመራን የሚሰጥ ዘርን ከመዝራት ጋር እኩል ነው።
ጸልየህ ከሆነና ምላሽ ለማግኘት ካቀድክበት ረዘም ላለ ጊዜ ስትጠብቅ ራስህን ካገኘህ ባለመታገስ በተፈተንክበት ጊዜ እየሰራ ስለሆነ እግዚአብሔርን አመስግን። ስለ ለውጥህ ምን እየተጠባበቅክ እና እየጠበቅክ እንደሆነ ለእግዚአብሔር ንገረው። ስትጠብቅ በማማረር እና በማጉረምረም ወጥመድ ውስጥ አትውደቅ። መልስህ በመንገዱ ላይ እንዳለ በደስታ ተማመን።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ተስፋ አትቁረጥ; እግዚአብሔር እየሰራ ነው ውጤቱንም በቅርቡ ታየዋለህ።