ሠላምን የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው

ሠላምን የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል፡፡ መዝ. 29÷11

እግዚብሔር ለእኛ ከሚነገረንና እኛን ከሚመራበት መንገድ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው በልብ ውስጥ ምስክርነት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በውስጣችን የትኛው ትክክል እንደሆነና የትኛው ትክክል እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ከአእምሮ እውቀት ይልቅ የውስጠኛው እውቀት (የውስጥ ምስክርነት) በጣም የጠለቀ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ እውቀት በመንፈስ የሆነ መረዳት ነው፡፡ ዝም ብሎ በቀላሉ ሰላም ማግኘትና ሰላም ማጣት ነው፡፡ ሰላም በማጣትና ሰላም በማግኘት የምናደርገውን እናውቃለን ደግሞ ማድረግ ያለብን የሌለብንን እናውቃለን፡፡

አንድ ወቅት ወሳኝ ውሳኔ መወሰን ከሚገባት ሴት ጋር አወራን፡፡ የእርሷ ቤተሰብና ጓደኞች የየራሳቸው ምክር ለግሰዋታል፡፡ ነገር ግን እርሷ በራሷ በውስጧ ትክክለኛውን መልስ ማረጋገጥ ፈለገች፡፡ ምክንያቱም እንዲህ አይነት የሕይወት ልምምድ ስላላት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የተወሰነ የገቢ ማግኛ ሥራ ሰርታ ትተዳደር ነበርና ያንን ሥራ ትታ እቤት ከልጆቿ ጋር መሆን ፈለገች፡፡ በእርግጥ እንዲህ ያለ ነገር ጥብቅ የሆነ የገንዘብ መስተካከያና እራስን የመቀየር ውሳኔ ለሷ ያስፈልጋታል፡፡ ነገሮቹ ምንም እንኳን በስሜት ላይ ተፅኖና ጫና ቢፈጥርባትም እርሷ ግን ነገሩን ከእግዚአብሔር ማወቅ ስለፈለገች ከማንም ሰው ለመስማት አስፈላጊ ትክክለኛ ውሳኔ አደረገች፡፡

ሴትዬዋ በዚህ ወቅት ከዘመዶቿ ለሳምንታት በመለየትና በመራቅ እግዚአብሔርን በአምልኮና በምሥጋና በፊቱ በማሳለፍ የሚነገረውን እያደመጠች መረዳትና ሠላም ወደ ልቧ ሲፈስ በእርግጥ ንግዱን መዝጋትና ሥራውን መተው ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ ተሰማት፡፡ በጥሞና ውስጥ ሆና ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን አረጋገጠች፡፡ ስለ ውሳኔዋም ከዚህ በፊት ተሰምቶዋት የማያውቅ ሰላም አገኘች፡፡

በጣም የሚገርመው ሰዎች ስለ ጉዳዮቻችን በጥሩ መንፈስ ሊነግሩን ቢችሉም በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ ማምጣት አይችሉም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ እኛ ጉዳይ ሲናገር ከፍተኛ ተፅዕኖ ይፈጥራል እግዚአብሔርን ጠይቅ እርሱ ሲናገር የውስጥ ሰላምና የውስጥ ምስክርነት በመስጠት ብቸኛ ነው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር ብቻ ሠላምን ይሰጣል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon