ሥልጣንህን ተጠቀም

ሥልጣንህን ተጠቀም

እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። – ሉቃ 10፡19

ኢየሱስ ከአስቸጋር ሁኔታዎች ጋር እንደማንገጥም ፈጽሞ ቃል አልገባልንም፡፡ በዮሐ 16፡33 እርሱ ያለዉ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አለፍ ብሎ አይዞአችሁ ነዉ ያለዉ ምክንያቱም እርሱ  ዓለምን አሸንፎአልና።

ይህ ጥቅስ የሚያስተምረን ዓለም በምታደርግብን ነገር ማዘን እንደሌለብን ነዉ፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ዓለም እኛን የሚጎዳበትን ኀይል አሳጥቶታል። በሕይወት እያለን ተግዳሮት ሊገጥመን ይችላል ነገር ግን በተረጋጋ አኳሀን እንገጥመዋለን፡፡

ሉቃ 10፡19 የሚለዉ እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም ነዉ፤ እዚህ ኢየሱስ እያለ ያለዉ ልክ እርሱ እንዳሸነፈዉ ዓለምን እንደምናሸንፍ ነዉ፡፡

ምንም እንኳ አንዳንዴ ለመፍታት ቀላል ያልሆኑ ተግዳሮቶችንና አስጨናቂ ሁኔታዎችን ቢገጥሙንም እኛ ነገሮችን በትክክለኛዉ መንገድ ለመያዝ ከሞከርን እንደማንጠቃ ኢየሱስ ተናግሯል፡፡ በኢየሱስ ያገኘሀዉን ሥልጣን ተጠቀምና መሰናክሎችህን ድል ንሳ!


የጸሎት መጀመሪያ

አባት ሆይ በክርስቶስ የሰጠኸኝን ሥልጣንና ሐይል እቀበላለሁ፡፡ ኢየሱስ እንዳደረገዉ የዚህን ዓለም መከራ እንዴት ድል እንድነሳ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon