እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። – መዝሙር 1፡3
መረጋጋት ሁላችንም የምንፈልገዉ ነገር ነዉ፡፡ ት.ኤርሚያስ 17፡8 እና መዝሙር 1፡3 ሁለቱም ክፍሎች ሥር እንደሰደደ ዛፍ እንድንረጋጋ ነዉ የሚያዙን፡፡ 1ጴጥ 5፡8 ሰይጣን እንዳይለያየን ሚዛናዊያንና በመጠን የምንኖር እንድንሆን ይመክረናል፡፡ እሱን ለመቋቋም የግድ ሥር የሰደድን፣ የተገነባን ፣ ጠንካሮች፣ የማንነቃነቅና እና በክርስቶስ ቁርጠኛ መሆን አለብን፡፡
ኢየሱስ ሥር የምንሰድበት ምርጡ አፈር ነዉ፡፡ የተረጋጋህ እንድትሆን ሁል ጊዜ ያዉ በሆነዉ ፣ ዘወትር ታማኝ በሆነዉ ፣ በንጉሱ፣ በቃሉ እዉነተኛ በሆነዉ በኢየሱስ ሥር መስደድ ትችላለህ፡፡ እርሱ አንድ ጊዜ አንድ መንገድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላ መንገድ አይደለም ፤ በሁኔታዎች አይለወጥም፤ ስለዚህ በእርሱ የተተከልህ ከሆንህ አንተም እንደዚያዉ ነህ፡፡
እግዚአብሔር በመከራ ጊዜ እንድንረጋጋ ኃይል ሊሰጠን ይፈልጋል፡፡ ሥር እንደሰደደ ዛፍ እንድንሆን ይፈልጋል ነገር ግን የት መተከል እንዳለብን የምንመርጠዉ እኛ ነን፡፡ ሥር የሰደድከዉ በዓለም ነዉ? በስሜትህ ነዉ? በዙሪያህ ባለ ሁኔታ ነዉ? ባለፈዉ ጊዜህ ነዉ? ወይስ ዛሬ በኢየሱስ ለመተከል ትመርጣለህ? በእርሱ እንድትደገፍ አነሳሳሃለሁ፡፡ የእርሱ መረጋጋት ዛሬ ያንተ ሊሆን ይችላል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ በአንተ መተከል እፈልጋለሁ፤ አንተ አትለወጥም ስለዚህ በሁሉም ሁኔታዎቼ ታረጋጋኝ ዘንድ በአንተ እታመናለሁ፡፡