ራስን መግዛት ለሁሉም ሁኔታ ይሰራል

ራስን መግዛት ለሁሉም ሁኔታ ይሰራል

እኔ አብን እለምናለሁ፤እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤አለም …ሊቀበለው አይችልም፡፡እናንተ ግን አብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ፡፡ – ዮሀ 14፡17

በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ለሁሉም ሁኔታ የሚሰሩ የተወሰኑ መልዕክቶች አሉ ራስን መግዛት ከእነዚህ አንዱ ነው፡፡በህይወታችን ያለው ችግር ምንም ይሁን ራስን መግዛት በሁሉም አቅጣጫ ይመጣል፡፡ራሳችንን በስርዐት የማንመራ ከሆነ ስሜቶቻችን ይመሩንና ህይወታችን ዘግናኝ ይሆናል።

ራስን መግዛትን መለማመድ ማለት በልክ መኖር ማለት ነው፡፡ በህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር ጥራት ያለው ውሳኔ መወሰንና እንዲፈጸም የሚያደርግ ስርአት ይፈልጋል፡፡ ብዙዎቹ ችግሮቻችን የስርዐት ዕጥረት ውጤት ነው፡፡ የገንዘብ ዕዳ የሚከሰተው የወጪ ልማዶቻችንን መቆጣጠር ሳንችል ስንቀር ነው፡፡ የጤና ችግር የሚከሰተው አመጋገባችንን መቆጣጠር ሲያቅተን ነው…የመሳሰሉት፡፡

ለመውጣት የሚከብድ የሚመስል ሁኔታ ውሰጥ ካላችሁ ብዙ ራስን መግዛት እና ስርአት ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና መንፈስ ቅዱስን በውስጣችን እንዲኖርና እንዲረዳን ሰጥቶናል፡፡

ዳግም ከተወለዳችሁ የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችሁ ራስን ከመግዛት ጋር ተሟልቶ አለ፡፡ አላሳደጋችሁት ይሆናል ነገር ግን ውስጣችሁ እንዳለ እወቁ፡፡ የሚያስፈልገው ነገር አላችሁ፡፡ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላችሁ ግንኙነት በኩል ራስን መግዛትን ለማዳበር ወስኑ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ራስን የመግዛት እና የስርአት ፍሬ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ በእኔ ውስጥ ባለው በመንፈስህ ሀይል አድርጊ/ግ ያልኸኝን አደርጋለሁ እንጂ በስሜቶቼ ቁጥጥር ስር አልውልም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon