ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም፡፡ – መዝሙር 34፡14
ሰላምን እንድናጣ የሚያደርገን ምንድን ነው? በርካታ ነገሮች ናቸው – ማርፈድ ፣ የመንገድ መዘጋጋት ፣ የተደፋ ቡና…. ለዚህ ነው በየዕለቱ በሰላም መራመድን ‹‹መለማመድ›› ያለብን ጠቃሚ የሚሆነው፡፡ ለምሳሌ መቼ ዝም ማለት እንዳለባችሁ እና በቀላሉ እንዳትቀየሙ ልታደርጉ መወሰን ትችላላችሁ፡፡ አንዳዴ ደግሞ መሳሳታችሁን እምባዛም ከቁብ ላትቆጥሩት ትችላላችሁ፡፡
ዝም ብላችሁ በመቀመጥ ሰላም ይሁን ብሎ መመኘት ፣ ክፉው እንዲሸሻችሁ በመመኘት ብቻ ወይም ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ በመመኘት ብቻ ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ሰላምን አጥብቃችሁ እሹ ይለናል፡፡ አዕምሯችሁን ሰላምን እንዲራብ አድርጉት፡፡
የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ውስጥ ፍሬ እንዲያፈራ ልቡ በሰላም በተሞላ እና ሰላምን የሚከተል ሰው ላይ መዘራት ይኖርበታል፡፡ ሁሉም አማኞች የሰላምን መንፈስ አጥብቀው መያዛቸው እግዚአብሔር በእነሱ ውስጥ እና እነርሱን ተጠቅሞ ቃሉ እንዲሰራጭ ይጠቀምበታል፡፡
በሕይወታችሁ ጥርመሳን እንዲኖር ትፈልጋላችሁ ይሁን እንጂ ጥረታችሁ ምንም ያሕል ብርቱ ይሁን መምጣት አልቻለም? ምናልባት ምክንያቱ በሰላም እየኖራችሁ ስላልሆነ ሊሀን ይችላል፡፡ ሰላምን እንድትሹ ፣ እንድትከተሏት እና በሙሉ አቅማችሁ የራሳችሁ እንድታደርጉት አበረታታችኋለሁ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
ጌታ ሆይ ዝም ሰላም እንዲያው በክስተት ይመጣል ብዬ መቀመጥን አልፈልግም ፡፡ በትጋት ሰላምን እከተላለሁ፡፡ የአንተን ሰላም እንዴት እንደምከትል አሳየኝ፡፡