ሰዉን ሳይሆን እግዚአብሔርን አስደሳች ሁን

ሰዉን ሳይሆን እግዚአብሔርን አስደሳች ሁን

ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። – ገላ 1፡10

እግዚአብሔር እንድትሆን የፈጠረህን ወይስ ሰዉን ለማስደሰት የምትኖር ሰዉ ነህ? በዚህ ጥቅስ መሰረት እግዚአብሔር ለእኛ ያለዉ ፈቃድ እርሱን እንድናስደስትና እንድንሆንለት የፈለገዉን እንድንሆን ነዉ፡፡

እግዚአብሔር እንድትሆን የፈጠረህን ልዩ ሰዉ ስትሆን አንዳንድ ትችቶች እንደሚገጥሙህ ጠብቅ፡፡ ይህ ሁሌ ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን የራስህን የጸና እምነት ተቃርነህ የምትቆም ከሆነ ራስህን መሆን አትችልም፡፡

እግዚአብሔር በተለየ መንገድ እንድትሄድ እንደሚፈልግ ልብህ እያወቀ ከሁሉም ህዝብ ጋር መጓዝን መምረጥ ማለት ሰዎች ስኬታማ የማይሆኑበት አንዱ ምክንያት ነዉ፡፡

እርምጃ እንድትወስድና እግዚአብሔር እንድትሆን የሚፈልገዉን ሰው እንድትሆን አበረታታሃለሁ፡፡ ሰዉ የጠቆመህን መንገድ ለመሄድ አትፍቀድ ፤ ልዩ ለመሆንና ትችት ለማስተናገድ ተበረታታ፡፡

እግዚአብሔር እንደተቀበለህና እንደሚወድህ አስተዉል፡፡  እርሱ ለምክንያት ነዉ የሰራህ አንተ የምታበረክተዉ አንድ ልዩ ነገር አለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ሰዎችን ለማስደሰት እየጣርኩ መኖር አልፈልግም፤ ልዩ ለመሆን ወስኛአለሁ፡፡ በአንተ ሞገስ ለመኖርና እንድሆነዉ የፈጠርከኝን ሰዉ መሆን እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon