ሳታቋርጡ ጸልዩ

ሳታቋርጡ ጸልዩ

አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፡፡ – ያዕ 4፡2

ሀያ አመት በፊት አከባቢ ከዚህ ቀጥሎ ያለው አረፍተ ነገር ህይወቴን ቀየረው፡አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፡፡የጽኑ ጸሎትን ህይወት የሚቀይር ሀይል እንዳውቅ ይሄ አጭር ጥቅስ በር ከፈተልኝ፡፡

በህይወቴ በዛን ወቅት ከብዙ የተለያዩ ነገሮች የተነሳ ተጨንቄ ነበር፡፡አገልግሎቴን ለማሳደግ፣ ባለቤቴ የተለያዩ ነገሮችን ለማስደረግ፣ልጆቼ በአንድ መንገድ እንዲሄዱ ለማድረግ፣ ሌሎች ሰዎች የምፈልገውን እንዲያደርጉ ለማድረግ ሁሉንም ነገር በራሴ ለማከናወን እየጣርኩ ነበር፡፡እንደምትገምቱት አልተሳካም!

እንደዛለ እና ተስፋ እንደቆረጠ ወጣት ክርስቲያን አንድ ቀን በራሴ ጉልበት መኖር ጥቅም እንደሌለው ተረዳሁ፡፡ችግሮቼን ወደ እግዚአብሔር መውሰድ እንዳለብኝ ገባኝ፡፡በሌላ ቃል አብዝቼ መጸለይ አስፈለገኝ ማለት ነው!

የእግዚአብሔርን ፍቅርና ለእኛ ያለውን ዕቅድ ስንረዳ ሊከፍትልን የሚፈልጋቸውን በሮች ማወቅ እንጀምራለን፡፡እነዚህን ነገሮች የምንረዳው ግን በቋሚነት የምናዋራው፣ድምጹን የምንሰማ ከሆነና ከእርሱ ጋር ባለን ግንኙነት ስር እየሰደድን ስንሄድ ነው፡፡

በማቴዎስ 7፡7 ላይ ኢየሱ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ፈልጉ ታገኙማላችሁ፤አንኳኩ ይከፈትላችኋል ብሏል፡፡

ብዙ ጊዜ አቅማችን ሲሟጠጥ ወደ ጸሎት ፊታችንን እናዞራለን ፡፡ነገር ግን ጸሎቶቻችን በፍጥነት ሳይመለሱ ሲቀሩ ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ዛሬ እንድትጸልዩ ብቻ ሳይሆን ሳታቋርጡ እንድትጸልዩ አበረታታችኋለሁ፡፡በራሳችሁ ነገሮችን ለማስተካከል እየጣራችሁ አትጨናነቁ፡፡በጸሎት ሁሉንም ለእግዚአብሔር ስጡ፡፡

አስታውሱ ስንፈልገው እንደምናገኘው ቃሉን ሰጥቶናል፡፡በሙሉ ልባችን በጸሎት እንፈልገው፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ችግሮቼን ወደ አንተ እንዳመጣ አሳስበኝ፡፡በራሴ ጉልበት መኖር ደክሞኛል፡፡የአንተን ምሪት እና አቅጣጫ አሳዪነት ያስፈልገኛል፡፡በየዕለቱ ስፈልግህ በአንተ እታመናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon