ሳትዘገዩ ጸልዩ

ሳትዘገዩ ጸልዩ

ወደስፍራውምደርሶ።ወደፈተናእንዳትገቡጸልዩአላቸው። (ሉቃስ 22:40)

ደቀመዛሙርቱ በጌተሰማኒ ኢየሱስን ሲጠብቁ በነበረበትጊዜ በተለያዩ ፈተናዎች ተፈትነዉ ነበር፡፡ ምናልባትም ሮጠዉ ለማምለጥም አስበዉ ይሆናል፣ ለመደበቅም፣ እንደጴጥሮስ ኢየሱስን እንደማያዉቅ እንደካደ ሁሉ ለመካድም ጭምር፡፡ ኢየሱስ ወደፈተና እንዳይገቡ እንዲጸልዩ እንጂ በፈተና እንዳይፈተኑ እንዲጸልዩ አልነገራቸዉም፡፡

ስህተትን ባለማድረጋችን እንዳልፈተን ሲሰማን ደስይለናል፣ ነገር ግን ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረዉ ፈተና በህይወታችን መኖር አለበት፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ካለን እምነት ማካከልአንዱ ስህተትን የማድረግ ፈተናን መቋቋም መቻላችን ነዉ፡፡ ኢየሱስ አስቀድመዉ እንዲጸልዩ ነገራቸዉ፤ ይህ ደግሞ ጫና ከመምጣቱ በፊት እሱን የሚቋቋሙበት ጥንካሬ ቀድመዉ እንዲኖራቸዉ ያደርጋቸዋል፡፡

አንድ ሰዉ ምግብ የመብላት ፍላጎቱ ላይ ችግር ካለዉ፣ ምግቡ ወደጠረጴዛ ከመቅረቡ በፊት ትክክለኛ ያልሆነዉን ምርጫዉን አይሆንም የማለትን ብርታት እንዲያገኝ መጸለይ አለበት፡፡ችግሩ ፊትለፊት ፈጦ እሰኪመጣ ከምግቦቹ በሚወጣዉ መልካም መዓዛ እስክንፈተን ለምን መጠበቅ ያስፈልጋል? ደካማ ጎናችንን አዉቀን በሱ ላይ ጥንካሬን እንድናገኝበየለቱ ብንጸልይ፣ ድልን እንደምናገኝ በእዉነት አምናለሁ፡፡ እኔ ረጅም ጊዜ የመጠበቅ ትዕግሰት እንደሌለኝ አዉቃለሁ፣ይሁን እንጂ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲገጥመኝ አስቀድሜ እጸልያለሁ፤ እሱም ይረዳኛል፡፡ እግዚአብሔር ኃይሉን እነደሚሰጠን ቃል ገብቷል፣ ይሁን እነጂ መጸለይ
ይኖርብናል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ ኃይልን በሚሰጥህ በእሱ በክርሰቶስ ሁሉንም ማድረግ ትችላለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon