ሳይታክቱ ማፍቀር

ሳይታክቱ ማፍቀር

ለተበደሉት የሚፈርድ ፣ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው፡፡እግዚአብሔር የታሰሩትን ይፈታል ፤ እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል ፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደረጋቸዋል ፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል ፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል ፤ ድሀ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላል ፤ የኃጢአተኞችንም መንገድ ያጠፋል፡፡ – መዝሙር 146፡7-9

በመጽሀፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔር ለተጨቆኑ ፣ ለተራቡ ፣ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ፣ አባት ለሌላቸው እና ለስደተኞች አስመልክቶ ስላለብን ሀላፊነት በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ስለ ብቸኞች ፣ ስለ የተተው ፣ ስለ ተረሱ እና ዋጋቢስ ተደረገው ስለተቆጠሩም ይናገራል፡፡ ስለተራቡ እና ስለተጨቆኑ ያስባል፡፡

በተለያዩ መንገዶች ሰዎች ይራባሉ፡፡ ሰዎች የሚመገቡት ምግብ ኖሯቸው ፍቅር እና አክብሮትን ይራባሉ፡፡ እግዚአብሔር በሀዘን የጎነበሱትን ያነሳል እንግዳዎችን ይጠብቃል አባት የሌላቸውን እና ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ይንከባከባል ፡፡ ይህን እንዴት ነው የሚያደርገው? በሰዎች አልፎ ነው የሚሰራው፡፡ ስለ ሌሎች የሚኖሩ የተሰጡ እና ራሳቸውን ያስገዙ ሰዎችን እግዚብሔር ይፈልጋል፡፡

እማሆይ ቴሬዛ አንድ ጊዜ እንዲህ አሉ ‹‹ ፍቅር ሀቀኛ እንዲሆን ትልቅ እንዲሆን አታስቡ ፡፡ የሚያስፈልገን ሳይታክቱ ማፍቀር ነው››

ብዙ ሰዎች እኛ እስክንደርስላቸው እና እስክናድናቸው ነው ባሉበት ሁኔታ ውስጥ የቆዩት ብዬ እገነዘባለሁ ፤ ያ የሚደርሰው ሰው ደግሞ አንተ/ቺ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ሳንታክት የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ አልፎ የሰዎችን ፍላጎት ፣ የስሜት ጉስቁሉና አካላዊ ጉዳት ለተጎዱ እና ለተሰበሩ እንዲደርስ እንፍቀድ፡፡ ሳንታክት እናፍቅር።

ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ሳልታክት እንዳፈቅር ኃይልን አስታጥቀኝ፡፡ ልብህን ስጠኝ እና ለተጎዱ ፣ አቅራቦት ለሚያስፈልጋቸው እንዴት መድረስ እንዳለበኝ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon