ስለራሳችን መዘንጋት

ስለራሳችን መዘንጋት

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶ ግን በእኔ ይኖራል ፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚእበሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው፡፡ – ገላቲያ 2፡20

ጳውሎስ ክክርሰቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ ይላል፡፡ በሌላ አነጋገር ለእግዚአብሔር መኖር ስለ እራሱ ማሰብ አቁሟል ማትለ ነው ፡፡ እኛም እንደ እርሱ እንድናደረግ እንበረታታለን፡፡

ይህን ስታነቡ ‹‹ለኔስ ማን ያስብልኛል?›› ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ማን ይጠነቀቅልኛል ? ይህ ጥያቄ ነው ለእግዚአብሔር እንዳንኖር የሚከለክለን፡፡

ምን እንደምናስብ ፣ እንደምንፈልግ እና እንደሚሰማን ማሰብ በጣም ቀላል ነው ነገር ግን ለራሳችን ለመኖር ማሰብ ግን በእርግጥ አድካሚ እና ባዶ የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ላይ አተኩሮ መኖር አስደናቂ እና ለሌሎች በምናደረገውም፤ ምን ያስፈልገኛል ምንስ ያሻኛል ከሚል ፍርሃት ነጻ ያወጣል፡፡

ደስታ የመኖሩ ምስጢር ራስህን ለራስህ ከማድረግ ይልቅ በመተው ነው፡፡ ትኩረትህን ከራስህ አንስተህ ወደ እግዚአብሔር ስታደርግ እርሱ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዴት እንደምትኖር ያሳይሃል፡፡

ቀናችሁን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር በመስጠት እንድትጀምሩ አበረታታችኋለሁ፡፡ ይህን በማድረግ ከእርሱ ጋር የሆነ ሕይወትን እንደትኖሩ በታማኝነቱ ያደርግላቹሃል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ አይኖቼን ፣ ጆሮዬን ፣ አንደበቴ ፣ እጆቼን ፣ እግሮቼን ፣ ልቤን ፣ ገንዘቤን ፣ ስጦታዎቼን ፣ ችሎታዬን ፣ ክፍሎቴን ፤ ጊዜዬን ፣ ጉለበቴን -ሁለንተናየየን እስጥሃለሁ፡፡ ለአንተ እንጂ ለራሴ መኖር አልፈልግም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon