ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ። – ማቴ 12፡37
በፍጹም ስለ ራስህ እኔ ትክክል አድርጌ አላዉቅም፣ አልለወጥም፣ አስጠላለሁ፣ የተረበሽኩ እመስላለሁ፣ አልረባም፣ እኔን ማን ሊወደኝ ይችላል? የሚሉ አሉታዊ ነገር እንዳታስብ ወይም እንዳትናገር። ማቴ 12፡37 የሚለዉ ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ ነዉ፡፡
ምሳሌ 23፡7 በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነው ይላል፡፡ በሌላ ቃል ስለራሳችን የምናስበዉና የምንነጋገርበት መንገድ ስለራሳችን የምናስበዉን ይገልጣል እናም ህይወታችንን ይነካል፡፡
በእግዚአብሔር ቃልና በክርስቶስ ኢየሱስ ባለህ ማንነት ተመስርተህ ስለራስህ መልካም ነገሮችን መናገር ያስፈልግሃል (ልክ እንደ ግል እወጃ)፡፡ ለምሳሌ “እኔ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነኝ፣ በክርስቶስ ተቀባይነት እንዲኖረኝ ተደርጌ ተሰርቼአለሁ፣ እግዚአብሔር የፈጠረኝና የሰራኝ በራሱ እጆች ነዉ እርሱ ደግሞ ስህተት አይሰራም”፡፡
ቀኑን መጽሐፍ ቅዱሳዊና አዉንታዊ እወጃ በማወጅ መጀመር እወዳለሁ፡፡ ወደ ሥራ እየነዳችሁ ወይም ቤት እያጸዳችሁ ይህንን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ በመስታወት ራሳችሁን እያያችሁ ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ “እግዚአብሔር ወዶኛል ተቀብሎኛልም እንደዚያዉ ነኝ” እንድትሉ አበረታታችኋለሁ፡፡ ስለራሳችሁ እግዚአብሔራዊና አዉንታዊ እዉነታ መናገር ስትጀምሩ እግዚአብሔር እንድትሆኑ እንደፈጠራችሁ ራሳችሁን በመሆን ትሳካላችሁ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ስለራሴ አሉታዊ ነገር በመናገር አሳልፌአለሁ፤ እንደወደድከኝና እንደተቀበልከኝ እዉነታዉን አዉጃለሁ፤ አንተ እንፈጠርከኝ ራሴን መሆን እችላለሁ፡፡