ስለገንዘብ ማሰብ ያለብን ሁነኛ መንገድ

ስለገንዘብ ማሰብ ያለብን ሁነኛ መንገድ

ለድኾች የሚሰጥ አይቸገርም፤አይቶአቸው እንዳላየ የሚሆን ግን ብዙ ርግማን ይደርስበታል። – ምሳሌ 28፡27

ገንዘባችንን ለማስተዳደር ያገኘሁት ሁነኛ መንገድ ገንዘባችንን መስጠት ነው፡፡ የገንዘብ ችግር በሚገጥመን ወቅት እንኳ መስጠታችንን አጥብቀን ልንቀጥልበት ይገባል፡፡ ይህ ገንዘባችንን የምናስተዳደርበት መፅሀፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤና መርህ ነው፡፡

በእግዚበሔር የገንዘብ መርህ መመራት እጅግ በጣም የሚቻልና ጠቃሚ ሃሳብ ነው፡፡ምናልባት መስጠት የማትችሉበት ወቅትና ሰዓት ላይ እንኳ ብትሆንም  ላለመስጠት አትወስኑ  እግዚያብሔር ታማኝና ባለባችሁ ሁሉ ሊረዳችሁ ይችላል፡፡

ሉቃ 19፡17 ላይ እንደሚናገረው እግዚያብሄር በማንኛውም ሁኔታ በትንሹም በትልቁም ነግር ሁሉ  ታማኞች እንድንሆን ነው የሚፈልገው፡፡ እንደዛ በምንሆን ግዜ ደግሞ በትልልቅ ነገሮች ላይ ስልጣን እንደሚሰጠን ይናገራል።

ምሳሌ 28፡ 27 ለድኾች የሚሰጥ አይቸገርም ይላል። በገንዘባችን ዙሪያ እግዘያብሔርን የምንታዘዝ ከሆነ፤ በተቸግርንበትም ጊዜ እንኳ የምንሰጥ ከሆነ እግዚያብሔር ይረዳናል የምንፈልገውንና የሚያስፈልገንን ሁሉ እግዚያብሔር ይሰጠናል፡፡ የምትስጡ ለመሆን ዛሬ ወስኑ ምንም አይቸግራችሁም፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ገንዘቤን ለአንተ ለመስጠት ዛሬ ወስኛለሁ በጣም ከባድ በሚሆኑብኝ ጊዜያት እንኳ የአንተ የገንዘብ መርህ እንደሚሰራ አምናለሁ፤አንተ ስለእኔ ያገባሃል አንተ መገኛዬ ነኽ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon