ስለ ሰውነታችሁ ጥንቃቄ አድርጉ

ስለ ሰውነታችሁ ጥንቃቄ አድርጉ

በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። – 1 ኛቆሮ 6፡20

አንዳንዶቻችን ሰውነታችንን መውደድና በአግባቡ መንከባከብ እንዳለብን አልተማርን ይሆናል፡፡ ያ ካልሆነ ጤናማ ህይወት ለመኖር ሦስት መሰረታዊ ትልልቅ ተግዳሮቶችን ማለፍ ይጠበቅብናል፡፡

ሰውነታችንን እንዴት አድርገን መንከባከብ እንዳለብን አናውቅም። መጥፎ አመጋገብና የተዛባ መረጃ ሰዎችን ስለትክክለኛው ነገርና ስለጤናማው አመጋገብ ያላቸውን ግንዛቤ ያበላሻል፡፡

ስለሰውነታችን ያለን አመለካከት በሚዲያ በምናያቸው ማስታወቂያዎች ተወሰኑ ናቸው። ልንደርስበት በማንችለው የውበት ልክ በመጣጣር እንጨነቃለን፡፡ ምንም እንኳን ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንደ ትክክለኛና መደበኛ ልኬት መስሎ ቢቀርብም ጤናማ ሰው ምን እንደሚመስል መለየትና መፈለግ ይኖርብናል፡፡

ልምምድ መስራት አሁን አሁን እንዳለፈበት ፋሽን እየታ ነው፤ ያለ ልምምድና ስፖርት ለመኖር ሁልጊዜም ያለንበትን ሁኔታ እንደ ምቾት እናየዋለን። መሄድ ከሌለበን በስተቀር በእግራችን ትንሽ መንገድ እንኳ አንሄድም፡፡ እውነታው ግን ሰውነታችንን ስፖርት ሳናሰራው ጤናማ አካል ሊኖረን አይችልም፡፡

በእነዚህ መሰናክሎች እየተቸገራችሁ ከሆነ እንዳትሸነፉ ዛሬውኑ ወስኑ፡፡ እግዚያብሔር ለሰውነታችን ተገቢውን እንክብካቤ እንድናደርግ ተናግሮናል፡፡ ስለዚህ በእግዚያብሔር ብርታት ላይ ለመደገፍና ጤናማ ህይወት ለመኖር ውሳኔ ይወስኑ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ሰውነቴን በሚገባ በመያዝና ጤናማ በመሆን አንተን ላከብርህ እፈልጋለሁ፤ በአንተ ኃይል ለውጥን ላደርግ እንደምችል አምናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon