አንድ ሰው በጣም አስፈላጊ ነው ብሎ ካሰበ እራሱን ያታልላል ፡፡ – ገላቲያ 6፡3
መጽሀፍ ቅዱሳችን ትዕቢትን በተደጋጋሚ ይቃወማል፡፡ የትዕቢትንም አደገኛነት በሚገባ ማጉላት አልችልም፡፡ ተመልከቱ ለትዕቢት እጅ ስንሰጠ ጠላታችን በእኛ ላይ ተጽዕኖ እንዲኖረው እየፈቀድን ነው፡፡ ራሳችንን አግዝፈን ስናስብ ሌሎችን ዝቅ እንድናደርግ ያነሳሳናል ፤ እግዚአብሔርን እንድንዘጋ ያደረገናል ፣ ከእግዛአብሔር ውጭ ምንም ነን የሚለውን እውነት ያስረሳናል፡፡
ይህን የመሰለ አቋም እና አስተሳሰብ በእግዚብሔር ፊት አጸያፊ ነው፡፡ ትዕቢትን በቅዱስ ፍርሃት ልንፈራው እና ደረስን ወይም ሆንን የምንለው ያ ልዩ ስፍራችን ከእግዚአብሔር ይቅርታ እና ፍቅር የተነሳ መሆኑንና በራሳችን ታላላቅ ነገሮችን በማድረጋችን እንዳልሆን ልንገነዘብ ይገባል፡፡
በአንድ ነገር ልህቀትን ያገኘን እንደሆነ ፤ የልህቀቱ ምንጭ እግዚአብሔር የሰጠን ጸጋ ብቻ መሆኑን ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ በራሴ አደረኩህት የሚል ሀሳብ በጀመርን ቅጽበት በትዕቢት ወጥመድ እንያዛለን፡፡
አስታውሱ እኛ የእግዚአብሔር ነን፡፡ ስለራሳችን የተጋጋነነን አመለካከት ከመያዝ ይልቅ በእግዚአብሔር ትልቅነት እና እርሱ ለኛ ባለው ፍቅሩ ላይ ይሁን ፡፡ በእርሱ ቅዱስ ጸጋ ብቻ እርሱ እንድንሰራው በጠራን ነገር ሁሉ ስኬታማ የምንሆነው።
ጸሎት ማስጀመሪያ
ጌታ ሆይ በሕይወቴ የሚገኝ መልካምነት እና ሕይወቴ ጭምር ከአንተ ናቸው፡፡ ራሴን በፊትህ ዝቅ አደረጋለሁ፡፡ ትዕቢቴን እናዘዛለሁ ፡፡ የተከናወነልኛ ልህቀትን ያገኘሁት በአንተ ጸጋ ደግነት ብቻ መሆኑን አውቃለሁ፡፡