ስልጣናትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነዉ

ስልጣናትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነዉ

ነፍስሁሉበበላይላሉትባለ ስልጣኖችይገዛ።ከእግዚአብሔርካልተገኘበቀርስልጣንየለምና፤ያሉትምባለስልጣኖችበእግዚአብሔርየ ተሾሙናቸው።(ሮሜ 13:1)

ስልጣንን የማክበርና የመገዛት አመለካከት በእለት ተእለት ህይወታችን ዘልቆ መግባት አለበት፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ደህንነታችን እና ደስታችን እነዲጠበቅ ስልጣናትን በሁሉም ቦታ አኑሯል፡፡እሱበመንፈስም ሆነ በስጋዊዉም አለም ስልጣናትን ሰጥቶናል፣ ስለዚህ ለነሱ መገዛት አስፈላጊ ነገር ነዉ፡፡ በባለስልጣንንም ሆነ የተቀመጠ ምልክትንም እንኳ ልናከበር ይገባል፡፡ “መኪና ማቆም ክልክል ነዉ” ተብሎ ምልክት የተቀመጠበትም ቦታ ካለ መኪና አታቁሙ፡፡ ቅርብ የሆነ የማቆሚያ ቦታ ለአካል ጉዳተኛ ብቻ ነዉ ከተባለ፣ ቦታዉ ረጅም የእግር መንገድ ቢኖረዉም!በተከለከለበት ቦታ አታቁም፡፡ “መጓዝ ክልክል ነዉ” ለሚል ቀይ የትራፊክ መብራት ቢበራ፣ አትጓዝ፡፡ በጣም ብትቸኩልም መንገድ አታቋርጥ፡፡ “መለፍ ክልክል ነዉ” በተባለበት መንገድ አትለፍ፡፡

እነዚህ ነገሮች ምንም ትርጉም የላቸዉም ብለህ ታስብ ይሆናል፡፡ በጣም ቀላል ነገሮችም ይመስላሉ፡፡ መልስ የሚሹ ትላልቅ ጥያቄዎችምይኖሩናል፡፡ ትላለቅ ችግሮቻችን ትናንሽ የሆኑ እሰኪመስሉን አንጠብቃቸዋለን፣ በእያንዳንዱ ቀናት ምርጫችን የሚሆነዉ ስልጣናትን ማክበር ወይም በህይወታችን ላይ ትልቅ ለዉጥአለማምጣትይሆናል፡፡

እንዲዚህ አይነቱ ከላይ የጠቀስኳቸዉ ለስልጣን አለመገዛትባህሪያት፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዳንሰማ የሚከለክሉ ናቸዉ፡፡ ምክንያቱም አግዚአብሔር ራሱ ነዉ ስልጣናትን በኛ መካከል ያኖረዉ እንድናከብራቸዉ ይፈልጋል፡፡ በዙሪያችን ያሉትን ስልጠናት ስናከብር እሱን እናከብራለን፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ እግዚአብሔርን በጥቂት ነገር ላይ ለመታዘዝ ጥንቃቄ አድርግ እነሱም በህይወትህ ላይ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ያመጣሉ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon