‹‹ …ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና። እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ›› (መዝ.6፡8 – 9) ።
ስንጸልይ እገዘዚአብሔር ይሰማናል መልስም ይሰጠናል፡፡ ይህንን ጥቅስ ለዛሬው ጊዜ ሲጽፍ እንደነበረው እንደ ዳዊት በድፍረት እንድንሆን በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደሆነ እስካወቅህ ድረስ በድፍረት ልትኖር ትችላለህ እንዲሁም በህይወትህ ያለውን ጦርነት ለማሸነፍ ሊረዳህ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው፤ አንተ ብቻህን አይደለህም፡፡
ከእግዚአብሔር ለመስማት ትልቁ መንገድ ነውና የመዝሙር መጽሐፍትን አንብበው፡፡ እርሱ በቃሉ አማካይነት ለእኛ ይናገረናልና በአሰቸጋሪ ጊዜያት መዝሙሮች ለየት ያለ ብርታትን ይሰጡናል፡፡ እነዚህን መዝሙሮች ስታነባቸው ለራስህ እንደምታነበብ አንብብ እንጂ ለሌላ አንድ ሰው እንደተደረገ አድርገህ አታሰላስለው፡፡ ነገር ግን ይህ እግዞአብሔር ላንተ በግልህ የላከልህ ደብዳቤ መሆኑን አስታውስ፡፡ እርሱ ለአንተ መልካም ዕቅድ እንዳለው እንድታውቅ ይፈልጋልና የሚፈትንህ የሚቃወምህ ነገር መኖሩ ምንም አንዳደለ ፣ እርሱ ካንተ ጋር እንዳለ እንድታውቅ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ዳዊትን ከነበሩት ጠላቶቹ ሁሉ ታደገው፤ አንተ በእርሱ ከታመንህና ድፍረት ካለህ እርሱ ላንተም ተመሳሳይ ነገር ደርጋል፡፡
እግዚአብሔር በህይወትህ እየሠራ እንዳለ እርሱን እያመሰገንህ ቀጥልና በሰላም ሁን፡፡ እኔ ደግሜ ላረጋግጥልህ የምፈልገው እግዚአብሔር ፈጽሞ አይረሳህም፡፡ እርሱ ለጸሎትህ መልስ ለመስጠት አይዘገይም፡፡እርሱ አንተ እንደምትጠብቀወ ፈጥኖ ባይመጣም፤ ነገር ግን አይዘገይም፡፡ ራዕይህን በፊት ለፊትህ ይዘህ ጠብቅ፣ ተስፋ አትቁረጥ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እግዚአብሔር እርዳታ ይልክልሃል፤ እርሱ ይደግፍሃል፤ ያድስሃል፣ ያበረታሃል፡፡