ገና ሥጋዊያን ናችሁና እስለ አሁን ድረስ ገና አትችሉም፡፡ – 1 ቆሮንቶስ 3፡3
ሁለት ዓይነት ክርስቲያኖች አሉ ፤ የትኛውን መሆን እንደምትፈልግ መምረጥ አለብህ፡፡ ሥጋዊ ወይስ መንፈሳዊ ክርስቲያን ትሆናለህ ?
ሥጋዊ ክርስቲያን ሰው አስደሳች እና ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ሰዎች ምን ይላሉ ብሎ የሚጨነቅ ሰው ነው፡፡ ያልበሰሉ እና የሚያደርጉት ሁሉ ከስሜት ፤ እንዲያው ወቅታዊ ስሜታቸው በሉ ወይ አድርጉ የሚላቸውን አድራጊዎች ናቸው፡፡ ዘወትር በጠብ ፣ ባለመርካት ፣ በቀላሉ በመበሳጨት እና ሰላም በማጣት ነው የሚያሳልፉት፡፡
መንፈሳዊ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ፍላጎት የሚከተል ሰው ነው፡፡ መንፈሳቸውን ዘወትር በቃሉ ይመግባሉ፡፡ እግዚአብሔር በሕይታቸው ሁሉ ጣልቃ እንዲገባ ይፈቅዳሉ፡፡ ከእርሱ ጋር ያላቸው ግኑኙነት እንዳይው አልፎ አልፎ ሳይሆን በየዕለቱ ፣ ሳምንቱ ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሳምንት አንዴ ብቻ ሳይሆን ትኩረታቸው እርሱ ነው፡፡
እስኳሁን ካልወሰናችሁ ክርስቶስን መከተል የሙሉ ጊዜ ትኩረታችሁ እንዲሆን አበረታታችኋለሁ፡፡ በምታደርጉት ሁሉ ጌታ ጣልቃ ይግባ፡፡ በፍቅር ፣ በቅንነት ፣ በትህትና በሰላም ሂዱ፡፡ የመንፈስን ፍሬ አፍሩ በእግዚአብሔር ሞገስ ተደሰቱ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ዘወትር በሥጋዊነት የሚመራ ሥጋዊ ክርስቲያን መሆን አልፈልግም፡፡ አንት የሚያስደስትህና በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ሰው መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ዛሬ ሥጋዊ ክርስቲያን ሳይሆን መንፈሳዊ ክርስቲያንን መሆንን መርጫለሁ፡፡