“ስጋ ደካማ ነው” እናንተ ግን መሆን የለባችሁም

…ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዬ፤መንፈስ ዝግጁ ነው፤ሥጋ ግን ደካማ ነው፡፡ – ማቴ 26፡41

ጌታ ከመሰቀሉ በፊት በነበረው ምሽት፣ደቀመዛሙርቱን በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሰብስቦ አንድን ነገር ጠየቃቸው ፡ወደ ፈተና እንዳትገቡ ሁላችሁ ነቅታችሁ ጸልዩ መንፈስ ብርቱ ነው ስጋ ግን ደካማ ነው፡፡(ማቴ. 26፡41)

ከደቀመዛሙርቱ የሚጠበቀው ነቅቶ መጸለይ ብቻ ነበር ነገር ግን በእንቅልፍ መውደቃቸውን ቀጠሉ፡፡ኢየሱስ ግን በሌላ በኩል ጸለየ እናም በመስቀል እንዲጸና መልአክ በመንፈስ አበረታው፡፡ደቀ መዛሙርት ግን አልጸለዩም-ተኙ-እናም ስጋ በእውነት ደካማ እንደሆነ ማረጋገጫ ሆኑ፡፡

ለእኔ ይሄ ታሪክ የጸሎትን ከፍተኛ አስፈላጊነት ማረጋገጫ ነው፡፡እንደ ክርስቲያን ያለ የዕለት ተዕለት ጸሎት እና ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ምንም እንደሌለን ማወቅ አለብን፡፡

ሁላችን እንደ “ደካማ ስጋችን” ፈቃድ ከመኖር ጋር እንታገላለን፡፡ነገር ግን ጸሎትን ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ስናደርግ እግዚአብሔር የስጋን ድካም እንድናሸንፍ በመንፈስ ያበረታናል፡፡

ዛሬ ብርታትን ለማግኘት እየተማመናቹበት ያላቹበት በምን ላይ ነው?በስጋችሁ?ወይስ ወደ እርሱ ስንቀርብ እግዚአብሔር በቸርነት የሚሰጠንን ሀይል እየሞከራችሁት ነው?


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ስጸልይ ስለሰጠኸኝ ሀይል አመሰግናለሁ፡፡ያለ አንተ ደካማ መሆኔን አውቃለሁ፣ስለዚህ የአንተ ጉልበት ለእኔ ከበቂ በላይ መሆኑን አውቄ ወደ አንተ በቋሚነት በጸሎት መቅረብን መርጫለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon