ስጦታዎችህን እንዴት እንደምታሳድግ

ስጦታዎችህን እንዴት እንደምታሳድግ

እነዚህ ሁሉ የዚያ የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰዉ እርሱ ራሱ እንደፈቀደ ይሰጠዋል፡፡ – 1 ቆሮ 12፡11

ዎች እግዚአብሔር የሰጣቸዉን ስጦታ እንዴት ማግኘትና ማሳደግ እንደሚችሉ ዘወትር ይጠይቁኛል፡፡ ከዚህ በታች እኔ የደረስኩበትን ጥቂት ጠቃሚ እርምጃዎችን ዘርዝሬአለሁ፦

  1. እግዚአብሔር በሰጠህ ጥንካሬ ላይ አተኩር፡ በራስህ ጠንካራ ጎን ላይ ማተኮር እግዚአብሔር በሕይወትህ ያስቀመጠዉን ጥሪ እንድታሟላ ይረዳሃል፡፡
  2. ስጦታህን ተለማመደዉ፡ ማድረግ የምትወደዉንና ማድረግ የምትችለውን አንድ ነገር ፈልግና ደጋግመህ አከናዉነዉ፡፡ ምን ሊከሰት እንደምችል ማወቅ ትፈልጋለህ? ስለራስህ ጥሩ ነገር ይሰማሃል ለምን የመሸነፍ ስሜት ስለማይኖርብህ።
  3. ልዩ ለመሆን ድፍረት ይኑርህ፡ ደስተኛ አለመሆን የሚመጣዉ አንተ ልዩ መሆንህን መቀበል ትተህ ሌሎች ሰዎችን ለመምሰል በምታደርገዉ ጥረት የተነሳ ነዉ፡፡
  4. ሂስ መቋቋም ተማር፡ በክርስቶስ ማንነትህን አዉቀህ በራስህ ተማመን፤ የሌሎችን ማረጋገጫ ለማግኘትና እይታቸዉን ሁሉ ለመቀበል ሳይሆን ለለዉጥ ሌሎችን ለመስማት ክፍት ሁን፡፡

እግዚአብሔር በአንተ ዉስጥ ታላቅነትን ዘርቷል፡፡ እስኪ ዛሬ እግዚአብሔር የሰጠህን ስጦታ በመጠቀም የምትጀምርበት ቀን ይሁን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የሰጠሀኝን ስጦታ ላለማዉና ላሳድገዉ እፈልጋለሁ ስለዚህ አንተን እንድከተል፣ ስጦታዎቼንና አቅሜን እንዳሳድግ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon