ሶስቱ በአንድ

ሶስቱ በአንድ

« …መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ»(1ኛዮሐ.5፡17)።

የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለአባት፣ ልጅና መንፈስ ቅዱስ ይናገራል፣ እርሱም እና እንደምናውቀው ስለ ቅዱስ ስላሴ የሚናገር ነው። በቃሉ ውስጥ «ልጁ» የሚል ቃል ባይጠቀምም ይህ «ቃል» የሚለው የሚያመልክተው ስለ ኢየሱስ ነው። ነገር ግን የሐንስ ምዕራፍ አንድ ላይ ኢየሱስና ቃሉ አንድና ተመሳሳይ ናቸው።

ስለስላሴ ስናስብ እንደምናስታውሰው እንርሱ ሶስት ናቸው ነገር ግን እንርሱ አንድ ናቸው። ይህንን በሂሳብ ስሌት አናሰላውም። ነገር ግን ይህ እንደመጽሐፍ ቅዱስ ትክክል ነው። በውስጣችን በሚኖር በመንፈስ ቅዱስ እኛም አባትንና ልጁን በውስጣችን አለን።

ይህ አስደናቂ እውነት ነው። ይህንን ለማስረዳት እጅግ አስፈሪ ነው። ይህንን በቀላሉ በልባችን እናምነዋለን። በመተንተን ለምረዳት አትሞክር። አንደ ትንሽ ህጻን ሁንና እመን ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ይህን እውነት ስለተናገረ። ሁሉም የእግዚአብሔር መለኮት አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በአንተና በእኔ እንዲሁም በማንኛውም ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝና ጌታ አድርጎ በተቀበለ ውስጥ ይኖራሉ። (ቆላ.2፡9-10 ተመልክት)።

ይህ እውነት እኛን ደፋር፣ ፍርሃት የለሽና በሚዛናዊነት ጠንካሮች ሊያደርገን ይገባል። ለእኛ ባለው በእግዚአብሔር እቅድ መሠረት ማንኛውንም ማድረግ የምንችለውን ነገር ማድረግ እንደምንችል ማመን ይገባናል ምክንያቱም ቅዱሱ ስላሴ ስለሚያስታጥቀን ነው። እርሱ የሚያስፈልገንን ሁሉና ከዛም በላይ ይሰጠናል። እግዚአብሔር ይወድሃል። ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ይሆናል። ለህወትህም መልካም ዕቅድ አለው። በእርሱ ህልውና በኩል በህይወት ልታደርገው የማስፈልግህን ማናቸውንም ነገር ለማድረግ አንተ ታጥቀሃል።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ የዛሬውን ቀን በድፍረት ውጣበት ምክንያቱም እግዚአብሔር አንተ ወደ ምትሄድበት ሥፍራ ሁሉ አስቀድሞ ወጥቶበት መንገድ አዘጋጅቶልሃል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon