ቀለል ለማለት መፍቀድ

ቀለል ለማለት መፍቀድ

በእግዚአብሔርም መንገድ ይዘምራሉ የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና። – መዝ 138፡5

በጣም የምጨነቅ ሰው ነበርሁ፡፡ ልጆቼ ምን እንደሚመስሉና ስለባህሪያቸዉ እጨነቅ ነበር ፣ ቤቴ ምን እንደሚመስል እጨነቃለሁ ፣ ሰዎች እንዴት እንዲሚያዩንና ስለእኛ ምን እንደሚያስቡ እጨነቃለሁ ፣ ባለቤቴን መምሰል አለበት ወደምለዉ ነገር ለመለወጥ እጨነቃለሁ ፤ ብቻ ያልተጨነኩበትን ነገር ማሰብ አልችልም፡፡ እጅግ ያስፈልገኝ የነበረዉ ግን ራሴን ቀለል ለማድረግ መፍቀድ ነበር፡፡

በየእለቱ ኑሮዬ እግዚአብሔርን እንዴት ማመን እንዳለብኝ አላዉቅም ነበር፡፡ በብዙ ነገር ከሚዛን ዉጪ ነበርሁ፡፡ በዓል ማድረግና ደስታ በሕይወታችን አስፈላጊ እንደሆኑ አልተገነዘብሁም ነበር፡፡ ያለ እነዚህ ነገሮች በመንፈሳዊ፣ በአእምሮና በስሜታችን ጤናሞች ልንሆን አንችልም! እርግጥ በዓል ማድረግ እጅግ አስፈላጊና እግዚአብሔር የፈጠረዉ ነገር እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር በዓል እንድናደርግ በቀጥታ አዞናል፡፡

ለቤተሰብህና ለዓለም ልትሰጠዉ የምትችለዉ ምርጡ ስጦታ ጤናማ አንተን ነዉ እናም በዓል ማክበርን የህይወትህ ቋሚ ነገር ሳታደርግ ጤናማ ልትሆን አትችልም፡፡ ዛሬ በዓልን በተመለከተ በሕይወትህ ያለዉን ጠቅላላ ከባቢ አየር ለዉጥ፤ ቀለል እንድትል ለራስህ ፈቃድ ስጥ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ዉጥርጥር ያልሁ እንድሆን አትተወኝ፤ ቀለል እንድል ለራሴ ፈቃድ እንድሰጥና በየዕለቱ መልካምነትህን እያሰብሁ በዓል እንዳደርግ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon