ወይስ መጽሐፍ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደተናገረ ይመስላችኋልን; ያዕቆብ 4÷5
የዛሬው ጥቅስ የሚጠቃልለው እውነታ፡- መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን መከበርን ይፈልጋል፡፡ በእርግጥ እርሱ ከእኛ ጋር ኅብረት ለማድረግ በጣም ይናፍቃል፡፡
በያዕቆብ 4÷4 መሠረት ከዛሬው ጥቅሳችን በመቅደም የቀረበው እንደምል ከእግዚአብሔር ይልቅ ለዓለማዊ ነገሮች ትኩረት ስንሰጥ ልክ እምነትን በማጉደል የተከለከለውን በማድረግ ቃልኪዳን እንደፈረሰች ሴት እኛንም ከዓለም ጋር እንዳደረግን ያያል፡፡ ከእርሱ ጋር በታማኝነት እራሳችንን ለመጠበቅ በእኛና በእርሱ መካከል ገብቶ ሊለያየን የሚፈልጉትን ነገሮች ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
ሥራችን እኛንና እግዚአብሔርን እንዲለያይ አድርገው ከሆነ ሥራውን ማጣት ይሻለናል፡፡ ገንዘብ ከእርሱ ለያይቶን ከሆነ እንዴት በትንሽ ገንዘብ እንዴት መኖር እንደምንችል መማርና ከእግዚአብሔር ከሚለዩን ነገሮች ሁሉ መቆጠብ አለብን፡፡ ስኬት ከሰማዩ አባታችን የሚያርቀን ከሆነ እየተሻልን ሳይሆን እየወረድን ነው፡፡ ጓደኞቻችን በሕይወታችን የመጀመሪያው ቦታ ከእግዚአብሔር በላይ የሚወስዱ ከሆነ ጓደኞቻችንን ብናጣ ይሻለናል፡፡
አብዛኛዎቹ ሰዎች ለመገንዘብ ያልቻሉት ነገር የሚፈልጉትን ነገር የማይቀበሉት በሕይወታቸው ለእግዚአብሔር የመጀመሪያ ቦታ ስለማይሰጡ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ ይቀናል፡፡ በሕይወትህ የመጀመሪያውን ቦታ ይፈልጋል እስካልሆነ ምንም የሚሆን ነገር የለም፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- እግዚአብሔር ከሕይወትህ ማንኛውንም ለእርሱ የሚሆነውን ቦታ የወሰደውን እንዲስወግድ ጠይቀው፡፡