ቀናችንን ለመጀመር ምርጡ መንገድ

ቀናችንን ለመጀመር ምርጡ መንገድ

ትረዳኝ ዘንድ ጎሕ ሳይቀድ ተነሥቼ እጮኻለሁ፤ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ። – መዝሙር 119፡147

ቀናችሁን እንዴት ነው የምትጀምሩት? ከአልጋችሁ በፍጥነት ተነስታችሁ በሰአት ከቤት ለመውጣት ትጣደፋላችሁ? ቴሌቪዥን ትከፍታላችሁ? የሰውነት እንቅስቃሴ ታደርጋላችሁ? ምንም አይነት የጠዋት ልምድ ቢኖራችሁ ዋና መጠየቅ ያለባችሁ ጥያቄ እግዚያብሔር በእያንዳንዱ ቀኔ ላይ መጫወት የሚፈልገው ሚና ምንድን ነው? የሚለውን ነው፡፡

ይህንን ለመረዳት በጣም እረዥም ጊዜ ቢፈጅብኝም አሁን ግን የተረዳሁትና ያወኩት ነገር ቢኖር እያንዳንዱን ቀኔን እግዚያሄር ስላደረገልኝ ነገር በማመስገንና ለሌሎች ሰዎች እንዴት በረከት መሆን እንደምችል እርሱን በመጠየቅ መጀመር እንዳለብኝ ነው፡፡

በእያንዳንዱ ጠዋታችሁ እግዚያብሔር ለእናንተ ያደረገው በጎ ነገር ላይ እንድታተኩሩ ላበረታታችሁ እፈልጋለሁ፡፡ከተለያዬ አደጋዎችና ተግዳሮቶች እንዴት እንዳሳለፋችሁ አስቡ፤ ለእንናንተ መልካም መሆኑን የሚያስብላችሁ መሆኑን ፀሎታችሁንም የሚሰማ መሆኑን አስቡ፡፡

በየእለቱ እግዚብሔር ላይ ትኩረት ማድረግን ስትለማመዱ እግዚብሔር በህይወታችሁ ውስጥ ሰላሙንና ደስታውን ይሰጣችኋል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ በእያንዳንዱ ማለዳዬ በአንተ ፊት በመሆን አንተን ለማመስገንና አንተን ለመፈለግ ወስኛለሁ፡፡ የአንተን ሰላምና ደስታን ከመቀበል የሚልቅ ምንም ነገር የለም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon