ቀጠሮ አክባሪ ሁን

ቀጠሮ አክባሪ ሁን

“እናንተ ትሹኛላቹ በፍጹም ልባችሁም ካሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ፡፡ ኤር 29፡13

በእግዚአብሔር ዕውቀት እንዳናድግ ከሚቃወመን የሥጋ ተቃውሞና የቸልተኝነት መንፈስ ለመላቀቅ መትጋት አለብን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜን የማሳለፍ መሠጠት በጣም ጥብቅ ጉዳይና ከሌለው ሁሉ የተለየ መስጠት መሆን አለበት፡፡

ካስፈለገ የኩላሊት ምርመራ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ ከጧት በ2፡00 ሰዓት ቢኖረኝ በመሠረቱ እኔ እንደነዚህ አይነቱን ቀጠሮ በዚህ ዓይነት ጊዜ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆንም፡፡ ምንም እንኳ ሕይወቴ የተመሠረተው የኩላሊት የሕክምና ክትትል ላይ የተመሠረተ ቢሆንም ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን ቀጠሮ የሚያዛባ ከሆነ በጣም ጠንቃቆች መሆን አለብን፡፡ የሕይወታችን ልቀት ላይ አብዛኛውን ጊዜ ተፅዕኖ የሚፈጥረው ከእርሱ ጋር በምናሳልፈው ጊዜ አንፃር ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ጊዜ በሕይወታችን ቀመር ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ቀጠሮአችን ችላ እንላለን ምክንያቱም እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይገኛል በማለት እግዚአብሄር እዛው አለልን በማለት ቀጠሮአችንን እንዘላለን ወይም እናድሰዋለን ከዚህም የተነሣ አንዳንድ ጊዜ በጣም አጣዳፊ ጉዳዮችን እንፈጽማለን፡፡ እኛ ብዙ ጊዜአችንን ከእግዚአብሔር ጋር ማሳለፍ ስንጀምር በጣም አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ሁኔታ ተፈጥሮ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ጊዜ የሚሻማ አይኖርም፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በምናጠፋበት ወቅት የእርሱ መገኘት ባይሰማንና ምንም ነገር የተማርነው ነገር ባይሰማንም እኛ አሁንም መልካም ዘር ወደ ሬት ጥሩ ምርት በሕይወታችን የሚታየውን እየዘራን መሆኑን መገንዘብ ጥሩ ነው፡፡ በጽናት ወደ እግዚአብሔር የቃሉ መረዳት ጫፍ ላይ ትደርሳለህ፣ ከእርሱ ጋር ሕብረት ወደ ማድረግ ደስታ፣ ለእግዚአብሔር ወደ መናገር እና ድምፁን ወደ መስማት ኅብረት ትመጣለህ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ቀጠሮህን ጠብቅ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon