ቃሉን ለማጥናት 4 ደረጃዎች

ቃሉን ለማጥናት 4 ደረጃዎች

መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና ሕጌን አትተዉ። – ምሳሌ 4፡2

ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት ማጥናት እንዳለባቸው ጠይቀዉኛል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ አራት ጠቃሚ ጉርሻዎች አሉ፡፡

  1. ሆን ብለህ ጊዜ ለይ፦ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር በየጠዋቱ ልገናኝ ቀጠሮ ይዤአለሁ ነገር ግን ይህ ላንተ ካልሰራ ሌላ ጊዜ ፈልግ። በየቀኑ ላይሆንም ይችላል፡፡ ብቻ አንድ ቦታ ጀምር ከዚያ በሕይወትህ የሚመጣዉን መልካም ፍሬ ታያለህ፡፡
  2. ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ዝግጅት አድርግ፦ በዚያ መገኘት የሚያስደስትህን ቦታ ምረጥ፤ በቤትህ ዉስጥ ብቻህን ልትሆን የምትችልበትን ክፍል፡፡
  3. ያሉህን ቁሳቁኦች ያዝ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የቃላት ዝርዝር (ኮንኮርዳንስ)፣ እስክብሪቶ እና ወረቀት ያስፈልጉሃል፡፡ በዚህ መንገድ ለማጠቀስና አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን መጻፍ ትችላለህ፡፡
  4. ልብህን አዘጋጅ፦ ንስሐ መግባት ስለሚያስፈልግህ ነገር እግዚአብሔርን አናግረዉ ከዚያ ከእግዚአብሔር ቃል መገለጥ እንዳታገኝ ከሚጋርድህ ነገር ነጻሆነህ በሰላማዊ መንገድ ጥናትህን ጀምር፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት ጊዜ ዉሰድ ምክንያቱም ህይወትህን መቀየር የሚችልና እግዚአብሔር የሚፈልገዉ ዓይነት ሰዉ የሚያደርግህ ሃይል ቃሉ ዉስጥ አለና፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ቃልህን ለማጥናት ጊዜ ለመመደብ አልሜአለሁ፡፡ በየዕለቱ ቃልህን እንድረዳ፣ ከቃልህ ጋር እንድስማማና ለቃልህ እዉነት እንድታዘዝ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon