ቃሉን መቀበልና መስጠት

ቃሉን መቀበልና መስጠት

አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ በእኔ ላይ የደረሰዉ  ነገር ወንጌል ባይበልጥ እንዲስፋፋ መርዳቱን ታዉቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ .. በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ካሉት ወንድሞች ብዙዎቹ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሃት፣ በድፍረት ለመናገር ብርታት አግኝተዋል፡፡ – ፊልጵስዩስ 1፡12-14

አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ካለን ተሳትፎ የተነሳ የጠላት ጥቃት ይደርስብናል፡፡ ማር 4፡17 ቃሉን ስለሚሰሙና ወዲያዉ ስለሚረሱ ሰዎች ይናገራል፡፡ ለጊዜው ነው እንጂ ሥር የላቸውም፥ ኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ ሲል ይናገራል፡፡

ሰይጣን ቃሉ እንደሚያጠነክረን ስለሚያዉቅ ለሌሎች ከማዳረሳችን በፊት ሊያስቆመን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ቃሉን በልብ መሰወርና ሰይጣን ሊሰርቅ ሲመጣ መቋቋም እጅግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ይህንን ስታደርግ ጠላት የሚያመጣዉ ሙከራ ሌሎችን ወደ ጌታ እንድታመጣ ያግዝሃል፡፡

ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ በእርሱ ምክንያት ሌሎች ወንጌሉን ያለፍርሃት ይመሰክሩ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲያልፍበት የመረጠዉ ብዙ መንገድ እንዳለ ይናገራል፡፡ በጳዉሎስ እስራት ጊዜ እንኳ በእግዚአብሔር ያለዉ መረጋጋትና እርሱን መጠቀሙ እውን ነበር፡፡

ሌሎችን ለማገልገል እየሄድን ከሆነ የተወሰነ የሚጎዳ ሁኔታ ይገጥመናል፤ ግን በእግዚአብሔር ተማምነን በእምነት ከቆምን እርሱ ወደ ድል ያመጣናል በዚያም ሂደት ለሌሎች ትልቅ መነቃቃት እንሆናለን፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በአንተና በቃልህ በየቀኑ መታመን እፈልጋለሁ፡፡ በመንገዴ ፈተና ሲመጣ እኔን እንዲያጠነክሩኝና ቃልህን ለሌሎች እንዳሰራጭ እንድትጠቀምበት እጸልያለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon