ቃላት እና ሀሳብ በቅርብ ይገናኛሉ

ቃላት እና ሀሳብ በቅርብ ይገናኛሉ

የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል ፣ ለከንፈሩ ትምህረትን ይጨምራል፡፡ ያማረ ቃል የማር ወላላ ነው ፤ ለነፍስም ጣፋጭ ለአጥነትም ጤና ነው፡፡ – ምሳሌ 16፡23-24

ምሳሌ 16፡ 23-24 ቃላችንና ሀሳባችን በጣም የተቆራኙ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በጣም የቀረቡ- እንደ መቅኒ እና አጥንት ናቸው ፤ ለመነጣጠል አስቸጋሪ ነው ( ዕብ 4፡12 ተመልከት) ፡፡ ከዚህ የተነሳ መልካም ቃላትን ለመናገር መልካም ሀሳብ ሊኖረን ይገባል፡፡

ሀሳቦቻችን ጌታ እና እኛ ብቻ የምንሰማቸው ፀጥ ያሉ ቃላቶች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ቃላቶች የውስጥ ሰዋችንን ፣ ጤናችንን ፣ ደስታችንን እና ባህሪያችንን ይጎዳሉ፡፡ ያሰብናቸውን ነገሮች መናገራችን የማይቀር ነው ፤ አንዳዴ ሞኝ ያስመስሉናል ነገር ግን በእግዚአብሔር መንገድ የምንኖር ከሆንን ሀሰባችንና ቃላችን ኑሮቻችንን የደስታ ያደርጉልናል፡፡

በሀሳብህ የዓለምን መንገድ እና አቅጣጫን እየመራህ በአፍህ የይምሰል መንፈሳዊ ቃላትን መናገር ፋይዳ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ፡፡ ወይ ሁለቱም መልካም ናቸው ካልሆን ደግሞ ሁለቱም አሉታዊ እና ሀጥያት ናቸው፡፡ በሁለቱ መካከል መካከለኛ የሚባል ስፍራ የለም፡፡

በክርስቶስ አዕምሮ መስራት ጀምር ከዚያም ፈጽሞ ያልኖርክበት ዓይነት አዲስን ኑሮ ውስጥ ትገባለህ፡፡ አስተሳሰብህን እንዲያስተካክልልህ ስትፈቅድ እና ጊዜ ስትወስድ ምን ልናገር ብለህ አትጨነቅም እንዲያው በተፈጥሮህ ንግግርህም ይሰተካከላል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ቃሌ እና ሀሳቤ የተገናኙ መሆናቸውን ተረድቻለሁ፡፡ እንዲያው በውስጤ የሌለውን ለይስሙላ እና ለማስመሰል አልፈልግም፡፡ እባክህን ንግግሬ ጣፋጭ እና መልካም እንዲሆን ሀሳቤን አስተካክልልኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon