በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፡፡ በእግዚአብሔርም ክብር ተስፋ እንመካን፡፡ ሮሜ 5÷2
እያንዳንዱ መንፈሳዊ ሕይወታችን የሚወሰነው በግል እምነታችንና ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ሕብረት ላይ ነው፡፡ በፍጹም የእርሱን ድምፅ ማሰማት መቻላችን ነው፡፡ በዚያ ኅረት እንደሰታለን፡፡ ምክንያቱም የኢየሱስ በመስቀል መሞት ነፃነት ሰጥቶናል፡፡ ባልተጋረደ ኅብረት ከሰማያዊ አባታችንና የእኛ እምነት ጥብቅ ኅብረት እንድናደርግ ያለማቋረጥ ከእርሱ ጋር ሕብረት እንዲኖረን አድርጓል፡፡
በሕይወቴ ኤፌ 3÷12 በጣም እወዳለሁ፡፡ ስለዚህም በቅርቡ ሳጠናው ነበርኩ፡፡ ‹‹በእርሱም ዘንድ ባለእምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትንና መግባት በእርሱ አለን›› ይላል፡፡ በዚህ ጥቅስ እንዳሰላሰልኩት በጣም የገረመኝ እኛ ተራ ሰዎች ሆነን ሳለ በነፃ በማንኛውም ጊዜ በፀሎት በእግዚአብሔር ፊት የመቅረብ እድል አገኘን፡፡ ድምፅን በማንኛውም ጊዜ ለመስማት በፈለግን ጊዜ ችለናል፡፡ ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያለፍርሃትና በሙሉ ነፃነት ማድረግ ችለናል፡፡ እንዴት ያስፈራል! የግል በእግዚአብሔር ዘንድ ያለን ያልተወሰነ የእርዳታ በርን ከእርሱ ዘንድ ይከፍታል፡፡ እንዲሁም ያልተገደበ ኅብረትን ከእርሱ ጋር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
ወደ እግዚአብሔር በሙሉ ድፍረት ና፡፡ እርሱ ይወድሃል፣ ያንተን ኅብረት ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም አንተን መስማት ብቻ ሳይሆን ለአንተም መናገር ይፈልጋል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ለመስማትና በመንፈሱ ለመመራት እርግጠኛ ሁን፡፡