በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ፤ ብሄድ እንኳ፣አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል። – መዝሙር 23፡4
አንዳዴ እግዚአብሔርን ያምናምነው የምንፈልጋቸውን ወይም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማግኘት ስለምናስብ ነው። ነገር ግን እውነተኛ የሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ከእርሱ ነገሮችን ለማግኝት ከማመን የዘለለ ነው፡፡ ከእርሱ ለማግኘት የምንሻቸውን ነገሮች ለማግኘት በምናልፋቸው ሂደቶች ውስጥ እርሱን መታመን መማር ይኖርብናል፡፡
በሕይወቴ ውስጥ ነገሮቼን እንዲያሳምርልኝ ትኩረት አድርጌ ‹ አምላኬ ሆይ ይህንን እፈልጋለሁ› ‹ ይህ እና ያኛው ያስፈልገኛል› ብዬ በእግዚአብሔር የታመንኩባቸው ጊዘዎች ነበሩ፡፡ ያኔ እግዚአብሔር የጠየኩትን ነገር ሁሉ ማግኘቴ እምብዛም በሕይወቴ አስፈላጊው ነገር እንዳልሆነ ያሳየኝ ጀመር፡፡
የእርሱ ፍላጎት የነበረው በሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ ሳልናወጥ ፣ በመልካም ልቦና እና ወጥነት እንዴት መራመድ እንደነበረብኝ እንድማርለት ነበር፡፡ ከአስቸጋሪ ሁኔታ መውጣት በፈለግን ቁጥር ላያወጣን ይችላል ነገር ግን በችግር ውስጥ በምናፍበት መንገድ ሁሉ አብሮን ይጓዛል፡፡
እግዚአብሔር ሊያወጣን ይገባል ብለን ከምናስበው ተግዳሮቶች ሁሌም አያወጣንም ነገር ግን ሁሌም ከእኛ ጋር ነው፡፡ ዛሬ በውጤት ላይ ከማተኮር ይልቅ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንደሆነ ተገንዘቡ፡፡ እርሱ ቅርብ ነው ፤ በምታልፉበት ሁሉ ከጎናችሁ እንደሆነ እመኑ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ አብረኸኝ ስለሆንክ ደስተኛ ነኝ፡፡ ነገሮችን እንደትሰጠኝ ብዬ ብቻ አልታመንም ነገር ግን ዘወትር በሚያጋጡምኝ ተግዳሮቶች ውስጥም ሆኜ እታመንሃለሁ፡፡