‹‹ … እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል›› (ዮሐ.4፡24) ።
በመንፈሳችን በኩል ከእግዚአሔር ጋር ህብረት እናደርጋለን፡፡ በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኢየሱስ እግዚአብሔርን በመንፈስና በእውነት እንደምናመልክ ተናገረ፡፡ ከእግዚአሔር ጋር የጠበቀ ህብረት የምናደርግበት አንዱ መንገድ ሙሉ በሙሉና ፍጹም እውነተኛ በመሆን ነው፡፡ ለማንኛውም ስለእኛ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ያውቃል፡፡ ሙሉ በሙሉ ታማኝ ላለመሆን ምንም የምናቀርበው ምክንያት አይኖርም፡፡ የሚሰማህን ስሜት፣ የሠራኸውን ስህተት፣ የምትፈልጋቸውን ፍላጎቶችን ሁሉ ንገረው፡፡ እንደመልካምና እውነተኛ ወዳጅ እንደሚሆን ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገር፡፡
እግዚአብሔር አንድ ነገር እንዳደርግ ሲፈልግና እኔም ያንን ነገር ማድረግ እንደማልፈልግ በታማኝነት የምናገርበት ብዙ ጊዜያት እንዳሉ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ለእርሱ በመታዘዝ ግን አድርገዋለሁ፣ ምክንያቱም እርሱን ስለምወደው ነው፡፡ ትክክለኛ ያልሆነና ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ህብረት ማድረግ ምንም የሚያመታው ውጤት የለም፡፡ አንድ ጓደኛዬ አንደ ጊዜ ‹‹ምንም እንኳን ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ ገንዘብ መስጠት እንዳለባት ብታውቅም፤ እርሷ ግን መስጠት እንደማትወድ ነገረችኝ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ታማኝ ነበረችና ለእርሱ እንዲህ አለች ‹‹እሰጣለሁ ነገር ግን በእውነት መስጠት አልፈልግም፤ ስለዚህ ለመስጠት እንድችል ፍላጎት እንዲኖረኝ እየጸለይኩ ነኝ›› ይህቺ ሴት በመጨረሻም በጣም ለጋሽና በደስታ የምትሰጥ ሆነች፡፡
እውነት ብቻውን አርነትን ያወጣል (ዮሐ.8፡32 ተመልከቱ)፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው፡፡ እርሱ የሚያደርገውን ይነገራል፤ የተናገረውን ያደርጋል፡፡ አንድ ስህተት በምንሠራበት ጊዜ ስለሠራነው ስህተት ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ታማኝ መሆን ይገባናል፡፡ ኃጢአትን በስሙ መጥራት፤ ስግብገብ ወይም ስስታም ከሆንን ስግብግብ ነኝ ብሎ መጥራት፤ ቀናተኛ ከሆንን ቀኛተኛ ነኝ ብሎ መናገር፤ የምንዋሽ ከሆንን ዋሾ ነኝ ብለን መጥራት አለብን፡፡ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን መለመንና በእምነት መቀበል አለብን፡፡ እግዚአብሔርን በምናመልክበት ጊዜ የምደርገውን ሁሉ በእውነትና በቅንንትና በታማኝነት በመንፈስ ማድረግ አለብን፡፡ ጓደኛችን እወነተኛ አለመሆኑ የሚሰማን ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ እንላለን ‹‹እውነተኛውን ማግኘት›› ማለትም ማስመሰልን እንዲያቆሙና ታማኝ እንዲሆኑ እየጠየቅን ነው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርም እንደዚሁ ዓይነት ተtመሳሳይ ነገር ይፈልጋል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እውነተኛውን ማግኘት