በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ መልካምንም አድርግ

በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ መልካምንም አድርግ

መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፡፡ – ኤፌ 5፡18

ሁላችንም ሰይጣን ሀጢአት እንድናደርግ እንደሚፈትነን እናዉቃለን ግን እግዚአብሔር ፈተነኝም እንላለን፡፡ እግዚአብሔር የሚፈትነንና የሚያነሳሳን መልካምን እንድንሰራ ነዉ፤ ይህንንም ሲያደርግ ሰይጣን አእምሮአችንን በማጥቃት ነገሩን እንዳናደርግ ምክናታዊያን ያደርገናል፡፡ ያን ከማድረግ ስንጎድል መልካምን አድርገን የምንባረክበትን ዕድል ከእኛ ይሰርቃል፡፡

መልካምን እንድናደርግ የሚቀርብልንን ፈተና ለመቃዎም ጎበዞች ነን ፤ ክፉ እንዳናደርግ የሚቀርብልንን ፈተና ለመቋቋም ግን ሰነፎች ነን፤ እንዲህ መሆን ግን አልነበረበትም፡፡

ያዕቆብ 4፡7 የሚለዉ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል ነዉ፡፡ ይህ ድርብ ነገር ነዉ ለእግዚአብሔር ሳትገዛ ዲያብሎስን መቋቋም አትችልም ደግሞም ድያብሎስን ሳትቃወም ለእግዚአብሔር መገዛት አትችልም፡፡

ኤፌ 5፡18 የሚነግረን በመንፈስ እንድንሞላ ነዉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ስትሞላ ለእግዚአብሔር ትገዛለህ ዲያብሎስንም ትቃወማለህ ዉጊያዉንም ታሸንፋለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በመንፈስ ቅዱስ ሙላኝ፡፡ የመንፈስህን መንገድ ለመከተል፣ መልካምን ለማድረግና ለሰዎች በረከት ለመሆን ራሴን ለአንተ አስገዛለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon