በማንኛውም ጊዜ መምጣት ይችላሉ

በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን። ኤፌሶን 3:12

እግዚአብሔር ያለፍርሃት ፣ በድፍረት እና በልበ ሙሉነት ወደ ፀጋው ዙፋን እንድንቀርብ ፈቃድ ሰጥቶናል። በመሠረቱ ፣ በኤፌሶን 3:12 ውስጥ በነፃነት ወደ እሱ እንድንቀርብ ያበረታታናል።

ከክርስቶስ ጋር ባለን ግንኙነት አማካኝነት ፣በመንፈሳችን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ነው። ነገር ግን ይህ ጥቅስ የሚነግረን ነገር በክርስቶስ ዘንድ የእግዚአብሔር ጽድቅ በመሆናችን ምክንያት እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እንደሚወደን እና እንደተቀበለን መተማመን እንደምንችል ሲሆን የእርሱን እርዳታ እና ይቅርታ ሲያስፈልገን በነጻ ይሰጠናል። በማንኛውም ሰአት ለሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ወደ እርሱ መቅረብ እንችላለን።

“ከመግባት እና ከመውጣት” ልዩ መብት ጋር ብንፈለግ በቀን ወደ 200 ጊዜ ወደ እሱ መሄድ እንችላለን። እግዚአብሄር በሩን እንድናንኳኳ ወይም “ግቡ” እስስክንባል ድረስ እንድንጠብቅ አይነግረንም።

“በማንኛውም ጊዜ እኔ ጋር መምጣት ትችላለህ። ይህን ታውቃለህ? በማንኛውም ሰዓት ፣ ቀንም ሆነ ማታ ፈቃድ ስላለህ ማንኳኳት እንኳ የለብክም። ዝም ብለህ ግባ!” የሚል ጓደኛ እንዳለህ አርገህ አስብ።

አሁን ዝም ብለህ አስብ… እግዚአብሔር ይህንኑ እየተናገረህ ነው። ይህ ማለት ጥንቃቄ ወይም ጥርጣሬ እንዳያድርብህ ወይንም የተፈቀደልህ ጊዜ ያለፈበት መስሎ እንዳይሰማህ ነው። ይህም ማለት ምንም እንኳን አንዳንድ ስህተቶችን ብትሰራ ወይም ማድረግ የሌለብህን ነገሮችን ብታደርግም እንኳን ለኃጢያቶችህ ንስሀ መግባት ፣ በኢየሱስ ደም ነፃ መሆን እና በድፍረት ወደ እርሱ መገኘት ትችላለእህ።

የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ አንተ መምጣት መቻሌ እና ሁል ጊዜም ከእኔ ጋር መሆንህን ማወቅ አስገራሚ ነው። ስለዚህ እድል በጣም አመሰግናለሁ ፣ ስላበረታታህኝም አመሰግንሃለሁ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon