በሞገስ ተመላለስ

በሞገስ ተመላለስ

ኀጥእ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራል። – ምሳ 28:1

አንዳንድ ሰዎች ሞገሳቸዉ ብዙ ነዉ ሌሎቼ ደግሞ እንደተወዳጅ የእግዚአብሔር ልጅ በሞገስ ለመኖር ይታገላሉ፡፡ እኔም እግዚአብሔር እንዴት በሞገስ መኖር እንዳለብኝ የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን እስካሳየኝ ድረስ ይህ ችግር ነበረብኝ፡፡ እነዚያን ቁልፎች ላካፍላችሁ እወዳለሁ፡፡

1. በፍርሃት መኖርን ተቃወም፡ ፍርሃት በመህበረሰባችን ዉስጥ ያለ ወራርሽኝ ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በዕብ 10፡ 38 ላይ በእምነት እንድንኖርና ወደ ፍርሃት እንዳንመለስ ያዘናል፡፡
2. እንቅፋቶችህን ወደኋላ አስቅራቸው አዲስ ነገር ሞክረህ ስላልተሳካ አንተ የወደቅህ አይደለህም፤ የምትወድቀዉ መሞከር ስታቆም ነዉ፡፡ ስህተት መስራትን አትፍራ፤ ስህተት ከሰራህ ወዲያዉ ተነስተህ ጉዞህን ቀጥል፡፡
3. ንጽጽሮችን አታንሳ፡ ራስህን ከሌሎች ጋር እስካነጻጸርክ ድረስ ሞገስ የማይታሰብ ነዉ፡፡ ሞገስና ተቀባይነት የሚመጣዉ ግን ማንነትህን ስትቀበልና የአቅምህን ሁሉ ስትሰራ ነዉ፡፡
4. እርምጃ ለመዉሰድ ፈቃደኛ ሁን፡ እግዚአብሔር እንድሰራዉ የሚፈልገዉ ይህ ነዉ ብለህ የምታምንበትን ነገር በልብህ ፈልግ ከዚያ ተግባራዊ አድርግ፡፡

ስለ እነዚህ አራቱም ቁልፎች ጸልይና እነርሱንም መኖር እንድትችል እንድረዳህ መንፈስ ቅዱስን ጠይቀዉ፡፡ በክርስቶስና በጸጋዉ መተማመን አለህ እናም በሞገስ ተሞላ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ! ሞገስ ከባህሪዮቼ አንዱ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ እነዚህን አራቱንቁልፎች እንድኖራቸዉ አቅም ስጠኝ፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon