በሠላም ሕይወትህን ዳኝ-

በሠላም ሕይወትህን ዳኝ-

የክርስቶስ ሠላም በልባችሁ ይብዛ ቆላ 3፡15

በተቻለኝ መጠን የሕይወቴን መንገድ በሠላም ለመሮጥ እሞክራለሁ፡፡ በግብይት ወቅት ነገር ሠላም ካልሠጠኝ አልሸምትም፡፡ በውይት ወቅት ሠላሜን ከነሣኝ ዝም እላለሁ፡፡ ውሳኔ ለማድረግ ስፈልግ አማራጮችን በመመልከት የትኛው ሠላም እንደሚሰጠኝ እመለከታለሁ፡፡ የተለያዩ ድምፆችን በመስማት ወቅት የትኛው መልዕክት የእግዚአብሔርን ሠላም በልቤ ውስጥ እንደመሰጠኝ አደምጣለሁ፡፡

በሕይወቴ የተማርኩት ሠላምን በሕይወታችን ስናድስ የሕይወታችን ኃይል እንደሚታደስ ነው፡፡ ሠላም በሕይወታችን በሌለ ጊዜ ከፍተኛ ስህተት ልንሰራ እንችላለን፡፡ በምንም ሁኔታ ቢሆን ያለሠላም መንቀሳቀስ ከንቱ ልፋት ነው እላለሁ፡፡ ሠላም ውስጠኛው የልብ ማረጋገጫ እግዚአብሔር ለእኛ ውሳኔ የሚሰጥ ምልክት ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን የሚመራው በሰላም ነው፡፡ የዛሬው ጥቅል የሚለው ሠላም ልክ እንደ ዳኛ የቱ መልካም እንደሆነ የትኛው መልካም እንዳልሆነ ያስረዳናል፡፡ ሠላም ከሌለ ሁሉም ከንቱ ነው፡፡ ለምንወስነው ነገርና የመጨረሻ ድምዳሜ በውስጣችን ለሚነሳው ጥያቄ ሁሉ የስሜት የአእምሮና የነፍሳችንን ሕግ በቀጣይነት በሕይወታችን ማድረግ አለብን፡፡

እራሳችንን ማሰልጠንና ማለማመድ ያለብን የውስጥ ማንነታችን ስሜት ከውስጣችን ሲከሰንና ሲመሰክርልን ውስጣችንን መታዘዝ መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህ መልክ ሠላም እየሰጠንና እየነሣን በትክክለኛ መንገድ ላይ መሆናችንንና አለመሆናችንን ያረጋግጣል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ዛሬ ሠላም የሕይወትህ ዳኛ ይሁንልህ፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ስትሆን ሠላም ታገኛለህ፣ ከትክክለኛው መንገድ ስትስት ሠላም ይርቅሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon