በስሙ መጸለይ

በስሙ መጸለይ

በዚያ ቀን ከእኔ ምንም አትለምኑም፤ እዉነት እላችኋለሁ፤ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል፡፡ እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ለምኑ ትቀበላላችሁ፤ ደስታችሁም ሙሉ ይሆናል፡፡ – ዮሐ 16:23-24

ናሹ ልጃችን ገና ትምህርት ቤት በነበረ ጊዜ እኔና ዳዊት ስንጓዝ አብረዉት የሚሆኑ ሰዎች ነበሩን፡፡ እነዚያ እኛ በማንገኝበት ጊዜ ልጃችንን የሚጠብቁልን ሰዎች ልጃችን የህክምና እርዳታ ካስፈለገዉ ልክ እንደ እኛ ሆነዉ በልጃችን ጉዳይ ላይ እንዲወስኑና የእኛን ስም እንዲጠቀሙ ህጋዊ ሰነድ ፈርመንላቸዉ ነበር፡፡

ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱና እርሱን ለምናምን ሁሉ ያደረገዉ ልክ እንደዚያዉ ነዉ፡፡ እንዲህ ብሏል በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እግዚአብሔር ያደርግላችኋል፡፡ ይህ እኔና እናንተ በስሙ የተቀበልነዉ ሥልጣን ነዉ፡፡

ስሙ ቦታዉን ይወስዳል፤ ስሙ እርሱን ይወክላል፡፡ በስሙ ስንጸልይ ልክ እርሱ ይጸልይ እንደነበረዉ እያደረግን ነዉ፡፡ ይኼ ዕድል ለማመን የሚከብድ ይመስላል ግን ማመን እንችላለን ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚያ ይለናልና፡፡ ስለዚህ የክፉን ስራ ለመቋቋምና የእግዚአብሔርን በረከት ወደዚህ ዓለም ለማምጣት የኢየሱስን ስም ሥልጣን ተጠቀም፡፡


የጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ጸሎቴን እየሰማህ እንደሆነና ልትመልስልኝም ዝግጁ እንደሆንክ አምኜ በኢየሱስ ስም በድፍረት እጸልያለሁ፡፡ በልጅህ ስም ለመጸለይ ስላገኘሁት ታላቅ ዕድል አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon