በስሜት ፈተናችን ወቅት በእግዚአብሔር እንታመን

በስሜት ፈተናችን ወቅት በእግዚአብሔር እንታመን

እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፤ ፈቃድህ ከሆነ፣ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም። – ሉቃ 22፡42

መንፈስ ቅዱስን የሚከተል ጠንካራ ክርስቲያን ወደ መሆን በአንድ ጀንበር የሚታደግ ጉዳይ ሳይሆን የሂደት ውጤት ነው፡፡ ቀስ በቀስ ፤ ከአንድ ልምምድ ወደ ሌላ ልምምድ እየተሸጋገርን ፤ እግዚአብሔር ሊያሳድገን ባዘጋጀው የስሜቶቻችን ፈተናዎች እና ማለፊያዎቻችን በመሄድ የሚደረሰብት ነው፡፡

እግዚአብሔር ስሜታችንን ለማነሳሳት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንድናልፍ ይፈቅዳል፡፡ ይህን በማድረጉም እኔ እና እናንተ እንዴት ያለ የሚዋዥቅ ስሜት እንዳለን እንድንገነዘብ እና የእርሱ እርዳታ እንደሚያስፈልገን እንረዳለን፡፡

ኢየሱስ ለእኛ ጥሩ ማሳያ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ለሀጢኣታችን ከመሞቱ አንድ ቀን አስቀድሞ ከባድ በሆነ የስሜት ማዕበል ውስጥ እያለፈ ነበር፡፡ መሞት አለፈለገም ነበር ይሁን እንጂ ስሜቱን ከማስተናገድ ይልቅ ‹‹የኔ ፈቃድ ሳይሆን ያነተ ፈቃድ ትሁን ››ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ የትኛውም ነገር በቅጽበት ወደ መሻሻል አይመጣም ነገር ግን ኢየሱስ ያለፈበት ፈተና ታላቅ ቢሆንም እንኳን በስተመጨረሻ ድልነሺ ነበረ፡፡

እናንተም የስሜት ፈተናችሁን ማለፍ ትችላላችሁ፡፡ ኢየሱስ በስሜቱ አልተነዳም ፤ እናንተም መነዳት የለባችሁም፡፡ ነገሮች ስሜታችሁን ሲጫኗችሁ፤ ቆም በሉ እና እንደ ይሄንን አጋጣሚ በመውሰድ እና በእግዚአብሔር በፍጹም አምናችሁ ተራመዱ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ በስሜት ፈተና ውስጥ ባለፈኩ ጊዜ በአንተ መታመን እንደምችል አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ምሳሌ አድርጌ ‹‹የኔ ፈቃድ ሳይሆን ያነተ ፈቃድ›› ትሁን እላለሁ፡፡ አንተ ለኔ የሚሻለውን ታውቃለህና በፍጹም እታመንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon