በስራ ብዛት ከጥቅም ውጪ አትሁኑ

በስራ ብዛት ከጥቅም ውጪ አትሁኑ

“እናንት ሸክም የከበዳችሁ እና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ፡፡ቀንበሬን ተሸከሙ፤ከእኔም ተማሩ፤እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀላል ነውና”፡፡ – ማቴ 11፡28-30

በመጀመሪያዎቹ ከጌታ ጋር የነበሩኝ እርምጃዎች እርሱን ለማገልገል በጣም ጉጉ እና ዝግጁ ነበርሁ፡፡ብዙም ደስ ለማይሉኝ ነገሮች ውስጥ ሁሉ እገባ ነበር፡፡ የዛ አንዱ ውጤት ቶሎ ምን ለመስራት እንደተቀባሁ ማግኘቴ ነው፡፡

በስራ ብዛት ከተወጠረው ህይወቴ የተነሳ ከእግዚአብሔር ጋር በቋሚነት ጊዜ አላሳልፈም ነበር፡፡ለእግዚአብሔር መልካም ነገሮችን እያደረግኩለት ነበር ነገር ግን በሂደቱ ውስጥ እርሱን ረስቼው ነበር፡፡ከዚህም የተነሳ ብዙ ጊዜ የስጋን ስራ ስለሆነ የምሰራው የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይሰማኝ ነበር፡፡

“የስጋ ስራ” ማለት የእግዚአብሔር ሀይል በውስጣችን ሳያልፍ የምናደርጋቸው ነገሮች ናቸው፡፡ከባድ ናቸው፣ያደርቁናል እናም ምንም አይነት ደስታም ሆነ እርካታን አያመጡም፡፡ብዙውን ጊዜ መልካም ነገሮች ናቸው ግን “እግዚአብሔራዊ” አይደሉም፡፡

ሰዎች እግዚአብሔርን በራሳቸው ጥረት ለማገልገል በሚያደርጉት ትግል ውስጥ በሀይማኖታዊ ልምምዶች ከጥቅም ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ኢየሱስ ግን ለእኛ የሞተው የማያቋርጥ ድርጊቶች ውስጥ እንድንጠመድ አይደለም…የሞተው በእርሱ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር አንድ እንድንሆን ከዚህም የተነሳ ደግሞ ከእግዚአብሔር አብ፣ከእግዚአብሔር ወልድ እና ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ጥልቅ እና የግል ግንኙነት እንዲኖረን ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን ዛሬ የተወሰነ የስጋ ስራ ማስወገድ ትፈልጋላችሁ?


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ መልካም ስራዎችን መስራት አንተን በእውነት ማወቅን በጭራሽ ሊተካው እንደማይችል ተረድቻለሁ፡፡የማይጠቅሙ ድርጊቶችን ወደጎን ትቼ ከአንተ ጋር ብዙ ጊዜ ሳሳልፍ እረፍቴን በአንተ እንዳገኝ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon