እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት የተሰጠው ተስፋ አሁንም የተጠበቀ ስለ ሆነ፣ ከእናንተ ማንም ለዚያ ሳይበቃ እንዳይቀር እንጠንቀቅ። (ዕብራውያን 4:1)
ስለ ጽድቅ ሳስተምር፣ የሚከተለውን ምሳሌ መጠቀም እወዳለሁ፣ አንተም እንድትሞክረው እጠይቅሃለሁ። ወንበር ላይ ተቀመጥ፣ ከዚያም ወንበሩ ላይ ለመቀመጥ ሞክር። ያ ሞኝነት እንደሚመስል አውቃለሁ፣ ምክንያቱም ቀድሞውኑ በወንበሩ ላይ ተቀምጠሃል። ወንበር ላይ ከተቀመጥክ በኋላ፣ እንተ ካለህበት የበለጠ ወደ የትም መሄድ አትችልም።
ይኸው ሀሳብ ለጽድቅ ይሠራል። ኢየሱስ መስዋዕት ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት አጽድቆናል፤ እናም እርሱ ካጸደቀን የበለጠ እራሳችንን ለማጽደቅ ምንም ማድረግ አንችልም። ባህሪያችን ሊሻሻል ይችላል፣ ነገር ግን በኢየሱስ በኩል ጽድቃችንን ሙሉ በሙሉ እስክንቀበል ድረስ ሙሉ አይሆንም። ኢየሱስ በጽድቅ ወንበር ላይ አስቀመጠን እናም ዘና ማለት እና ቀድሞውኑ የሆንነውን ለመሆን መሞከር ለማቆም መማር አለብን። ከክርስቶስ በቀር የቱንም የሚያክሉ መልካም ተግባራት በእግዚአብሔር ፊት ሊያጸድቁን አይችሉም። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ሲያስረግጥ በክርስቶስ እንዲሆን እና እንዲታወቅ ደግሞም የራሱ የሆነ ጽድቅ የሌለው ነገር ግን በክርስቶስ በማመን የሚገኝን ጽድቅ እንዲሆንለት ጸለየ። (ፊልጵስዩስ 3፡9ን ተመልከት) ።
እኛ እራሳችንን ለማጽደቅ ምንም ማድረግ እንደማንችል ደግሞም ለእግዚአብሔር ምንም ነገር ማረጋገጥ እንደማያስፈልገን በእውነት ስንረዳ፣ ኢየሱስ በሰጠን የጽድቅ ስጦታ ላይ ማረፍ እንችላለን – ያ ደግሞ እርሱን በድፍረት እንድንጠይቅ እና እግዚአብሔር ሊመልስልን ባለው ፍላጎት እንድንተማመን ያደርገናል። እግዚአብሔር ጸሎቴን የሚሰማኝ ወይም የሚመልስልኝ እኔ መልካም ስለሆንኩ አይደለም። እርሱ መልካም ስለሆነ ይሰማኛል ደግሞም ይመልስልኛል!
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እግዚአብሔር በገዛ እጁ ስለፈጠረህ ማንነትህን ውደደው።